ቀሲስ ታምራት ውቤ

ቀሲስ ታምራት ውቤ

ነገረ አእዋፍ

መጽሐፈ ዘፍጥረት የአምስተኛውን ቀን ፍጥረታት ሲተርክ “እግዚአብሔርም አለ፡- ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፤ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈርም በታች ይብረሩ” በማለት ይጀምራል፡፡ ዘፍ 1፡20 አእዋፍ ጌታ እግዚአብሔር ከውኃ ከፈጠራቸው መካከል ናቸው፡፡ ከውኃ ተፈጥረው የተሰጣቸው ተፈጥሯዊ ጸጋ ደግሞ “ከምድር በላይ”…

ኑሮን ስለ ማቅለል

ኑሮን ስለ ማቅለል | ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.| ✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ “ሰው ለምቾትና ለተቀማጠለ ሕይወት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ለንስሓ ያለው ቁርጠኝነት ይቀንሳል፡፡ ” (ፍና ቅዱሳን – ገጽ 51) ብዙ ጊዜ በምቾት የተቀማጠለ ሕይወትን እና ኑሮን ቀለል ባለ…

መሆን እና መኖር

ቅዱስ ጴጥሮስ በደብረ ታቦር ተራራ የጌታችን መልኩ ተለውጦ ሲያበራ፤ ልብሱም በምድር አጣቢ ሊያነፃው ከሚችለው በላይ ነጭ ሲሆን፤ ሙሴና ኤልያስም መጥተው ከጌታ ጋር ሲነጋገሩ አይቶ የመጣለትን ሀሳብ የገለጠበት ቃል ነው ” በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው”። አባቶች ቢርበንና ቢጠማን ሙሴ መና…

ታላቁ ሠርግ 

ሙሽራው ሠርግ ማድረግ ሸቶ ከሕዝብ፣ ከነገድና፣ የተለያየ ቋንቋ ከሚናገር ወገን ሚስት ያጩለት ዘንድ ሽማግሌዎችን ላከ። ሽማግሌዎቹም የሙሽራውን ማንነት ለሰብአ ዓለም በተለያየ ኅብረ አምሳልና ቃል ገለጡ። ከባቢሎን እስከ ግብፅ ፣ ከኢየሩሳሌም እስከ ግሪክ፣ ከፋርስ እስከ ሮም ለሙሽራው ራሳቸውን ለማቅረብ ፈቃደኞች ለሆኑ…

የፍቅርና የጥላቻ መሥዋዕት

በሰው አማካኝነት በቤተ ክርስቲያን ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ ሁለት ዓይነት መሥዋዕት ሲቀርብ ኖሯል፤ የፍቅርና የጥላቻ መሥዋዕት:: ይህ እንደምን ነው? ቢሉ ታሪኩን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደባት ከቤተልሔም ጀምረን እንመዛለን።  የጌታችንን በቤተልሔም መወለዱን የእንስሳት እረኞች “እንደ እንስሳ ሆነ” ተብሎ የተነገረለትን ሰውን ለመጠበቅ…

ክርስትናን ከዝርዝር ውስጥ አውጪው

የእግዚአብሔር ቃል የነካው ልብ በማያቋርጥ አለማረፍ ውስጥ ያርፋል። የያዘውን እያፀና የፊቱን ለመያዝ ይዘረጋል። ሁል ጊዜ ራሱን “ይህን ሁሉ ፈጽሜአለሁ፤ የሚጎድለኝ ምንድር ነው?” ሲል ይጠይቃል። ተስፋው የተረጋገጠ የሚሆነው ፍርሃት በገፋው ንስሐው፣ ልምድ በቃኘው ክርስትናው፣ ፍቅር በተለየው አምልኮቱ ሳይሆን “በእግዚአብሔር ቸርነት” ላይ…

   የወርቅ ቀለበት በእሪያ አፍንጫ

ገና በአፍላ ዕድሜው እግዚአብሔር በመረጠው ታላቅ ሕዝብ ላይ የነገሠው ጠቢቡ ሰሎሞን በልጅነት ጫንቃው ላይ የወደቀበትን ኃላፊነት እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ቢጨንቀው የበጎ ሥጦታዎች ሁሉ ባለቤት የሆነውን የአባቱን የዳዊትን አምላክ ጥበብን እንዲሰጠው ለመነ። ልዑሉም ከእርሱ በፊት ከእርሱ በኋላ የሚነሡ እንዳይተካከሉት ባለ ጠግነትንና…

ደም ላነሳት ደም ልገሳ

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ 12 ዓመት ታዳጊ የነበረችዋን የኢያኢሮስን ልጅ ከሕመሟ ለመፈወስ ሲጓዝ በመንገድ ብዙ ሕዝብ ያጨናንቀው ነበር። ከሚተራመሰው ሕዝብ የተወሰነው ተአምራት ሊያይ፤ ገሚሱ ሕብስት ሲያበረክት ጠብቆ ሊበላ፤ ሌላው መልኩን ሊያይ፤ ደግሞ ለበላይ አለቆች ያየና የሰማውን መረጃ ለማቀበል፤ የተቀረው ትምህርቱን…

የተዋጀንበት ምሥጢር

በሉቃ 15 ላይ በወንድሙ መመለስ አኩርፎ የነበረው ልጅ አባቱን እኔ ዘመኔን ሁሉ አገለገልሁህ ግን አንዲት የፍየል ጠቦት (በፈለጋችሁት ሥጦታ መስሉት) እንኳ አልሰጠኸኝም ሲለው “የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው” በማለት የእርሱ ዋጋ አብሮ በመኖር እንጂ በሥጦታ የተወሰነ እንዳልሆነ በመንገር አጽናንቶታል። ሰው…

እማዕሰረ . . . እግዚአብሔር ይፍታ !

ዛሬ ሰምቼው በጣም የወደድኩትና ሁልጊዜ ከማሰላስለው ሀሳብ ጋር የሚሄድ አንድ ቁም ነገር ላካፍላችሁ መልካም መስሎ ታየኝ። ታሪኩ እንዲህ ነው። አንድ የአራዊት ማቆያ ሥፍራን መጎብኘት የሚወድ ሰው የፈጣሪ ድንቅ ሥራ የሆኑ እንስሳትና አራዊትን እየተመለከተ ሲዘዋወር ትዕይንት (circus) ለማሳየት የሰለጠኑ እጅግ በጣም…