የተፈጠርነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ሰው ሆነን ወደ ምድር የመጣንበትን ዘመን፣ የተገኘነበትን ምድር፣ የወጣንበትን ማኅበረ ሰብእ እና ሌሎችንም ጉዳዮች የመረጠ እርሱ እግዚአብሔር ነው። አዳም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ በራሱ ምርጫ ራሱን ያስገኘ ማን አለ? አጭር ወይም ረዥም፣ ቀጭን ወይም ወፍራም፣ ነጭ ወይም ጥቁር ሆኖ ስለመወለዱ ከእግዚአብሔር ጋር የተማከረስ ማነው? ሁሉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተከናወነ ነው። ገበሬ ዘሩን በምድር ላይ በበተነ ጊዜ ምድሩን ለዘሩ የሚመርጥለት ገበሬው ነው እንጅ ዘሩ እንዳልሆነ ሁሉ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ምርጫ እንጅ በራሱ ምርጫ ወደ ዓለም ሊመጣ አይችልም። 

በዚህ መንገድ ወደ ምድር የመጣ የሰው ልጅ የሚኖረውም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መሠረት አድርጎ ነው። በማኅፀን በሠራን ጊዜ ለሕይወታችን የሚያስፈልገንን አንዳች ሳያጎድል ሠርቶ ከማኅፀን ስላወጣን በምድር ላይ ስንኖር የምንኖርበትን ትዕዛዝ ቢያዝዘን አንዳች እንደሚያጎድልብን ሳንጠራጠር አምነን እንታዘዝለታለን። በባሕር የሚኖሩትን በባሕር ለመኖር የሚያበቃቸውን፣ በየብስም የሚኖሩትን በየብስ ለመኖር የሚያስችላቸውን አካል ሰጥቶ ፈጥሯቸዋል። አካላችንን ከሥርዓተ ዓለም ጋር አስማምቶ ምንም የማይጠቅም አካል ሳይጨምር የሚበቃንን እና የሚያስፈልገንን ብቻ ሰጥቶ ወደ ዓለም እንድንመጣ ማድረጉ ለእኛ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመስጠት የሚያኖረን እርሱ ብቻ መሆኑን እንድናምን ያስገድደናል። 

ከዚህም የተነሣ ነው ሰባኪዎቻችን፥ በሰው እንዳንታመን “ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆችም አትታመኑ ነፍሳቸው ትወጣለች ወደ መሬትም ይመለሳሉ” መዝ 145፥3 ብለው ብለው መታመናችንን በሥጋዊና በደማዊ ፍጥረት ላይ እንዳናደርግ የመከሩን። 

ልንኖረው ከተፈቀደልን ሦስት ክፍል ካለው ኑሯችን የመጀመሪያውን ያለ እግዚአብሔር በቀር ከእኛም ሆነ ከሰዎች አንዳች ምክር የሰጠበት የለም። ከማኅፀን ከወጣንም በኋላ የምንኖረው ሁለተኛውን ክፍል ኑሯችንን ሲሆን ከማኅፀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ ራሳችንን በሰዎች ዕቅፍ ስለምናገኘው ነው መሰለኝ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ይልቅ በራሳችንና በሰዎችም ፈቃድ የመኖር ዝንባሌ ይታይብናል። 

በውስጣችን ባለው አድሮብን፣ ተዋሕዶን ከሚኖረው አምላካችን ይልቅ አጠገባችን ከጎናችን ባሉ ሰዎች ተስፋ እናደርጋለን። ይልቁንም በቤተ እግዚአብሔር ለሚኖሩ ሰዎች በሰው መታመን እንዴት ያለ አስቸጋሪ ነገር መሰላችሁ? 

ይህንን ያልሁት የዛሬውን መጻጉዕን ጉዳይ ሳስብ ቀድሞ የሚመጣብኝ እግዚአብሔር ሰዎችን ወድ ሚያድንበት ስፍራ ሂዶ ሰው መጠበቁ ስለሚያስገርመኝ ነው። የመጻጉዕን መዳን ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያዘገየበት በሰው ስለሚታመን ሳይሆን አይቀርም። “ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት” ዮሐ 5፥5 በሚለው የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የሚታየው ሀሳብ መጻጉዕ በእግዚአብሔር ደጅ እየኖረ በሰው የሚታመን በሽተኛ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ከሩቅ ቦታ አምጥቶ የመጠመቂያው ስፍራ ያደረሰው ማነው? ይሄ ሰው ይህንን ያኽል ዘመን እንዴት አንድ ሰው ወደ መጠመቂያው እንዲወርድ ሊረዳው አልፈቀደም? አብረውት በመጠመቂያው ስፍራ ተኝተው የሚሰነብቱ አንካሶችን በሽተኞች ከዳኑ በኋላ እንኳን ይህንን ሰው ወደ መጠመቂያው ስፍራ አውርደውት ድኖ እንዲመለስ እንዴት አላደረጉትም? እያልሁ ብዙ ጊዜ አስቤ አውቃለሁ። 

ይህ ሰው ከመጀመሪያው እምነት የጎደለው ነው። የዳኑት ሁሉ እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ሳይሆን ሰው ስላላቸው ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ነው። የመጣው የእግዚአብሔር መልአክ በወረደ ጊዜ በሚናወጠው ውኃ ውስጥ ገብቶ ተጠምቆ ፈውስ ለማግኘት ነው ነገር ግን በሃይማኖቱ ላይ የሰዎችን እርዳታ ካልተጨመረበት በቀር መዳን እንደማይችል በማሰብ ይሄንን ሁሉ ዘመን ሰው ሲፈልግ ነው የኖረው። በእግዚአብሔር ፊት ሆኖ ሰው መጠበቅ የሚያስገርም ነገር ነው። ለዚህም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ካዳነው በኋላ ራሱን ሳይገልጥለት በሰዎች መካከል ሆኖ የሄደው። እሱም ያዳነው ማን እንደሆነ ሊመረምር አልተመለሰም። ሰው ሲጠብቅ የኖረ ሰው እግዚአብሔር አዳነኝ ማለት እንዴት ይችላል? አይሁድ በጠየቁትም ጊዜ “ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” ነው እንጅ ያለው እግዚአብሔር አዳነኝ አላለም። 

እምነታችን ሳይጸናልን ገንዘብ ብንቀበል፣ ሥልጣን ብናገኝ፣ ጤና ቢኖረን፣ ጉልበታም ብንሆን፣ ውበትና ደም ግባት ቢስማማልን፣ ዓለምን በመላው የእኛ ማድረግ ብንችል ምንም ጥቅም እንደሌለው ተመልከቱ። 

መጻጉዕ ያዳነውን ትቶ አልጋውን ተሸክሞ መሄዱ ያሳዝናል። ከዚያች ቀን ጀምሮ ሰይጣን ዝም ብሎ ሊተወው አልወደደም። እስከ ዕለተ ዐርብ ድረስ ተከታትሎ ፍጹም ኃጢአት አሠርቶታል። በሕይወቱ ውስጥ ከሕማሙ ቀጥሎ ሌላ ፈተና ይዞበት የመጣው ፈውሱ ከእምነቱ በመቅደሙ ነው። ከዳነ በኋላ ከዐሥሩ ለምጻሞች እንደ አንዱ እግዚአብሔርን እያመሰገነ በቤተ መቅደስ ሊገኝ ይገባው ነበር እርሱ ግን ይህንን ሲያደርግ አልታየም። ያለ ሃይማኖት የሆነ ነገር ሁሉ ፈተናው ከባድ ነው። 

ከሁሉም ነገር በፊት ሃይማኖትህን እንዲያጸናልህ ለምን። ሕይወትህን ከሚገጥምህ ፈተና ሁሉ ጠብቆ ሊያኖራት የሚችል በልብህ ውስጥ ያለው ሃይማኖትህ ነው። ሁሉንም ነገር ከተቀበልህ በኋላ ከሁሉም አስቀድሞ እግዚአብሔርን ለማመስገን ጊዜ ይኑርህ። ንብረትህን ከመሰብሰብህ በፊት ልብህን ሰብስበህ አስብ። ቀጥሎ ለምትጓዝበት መንገድ የሚረዳህ ይህ ነውና። ዳዊት ጎልያድን በማሸነፉ “አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ” ብሎ ዘመረ እንጅ በራሱ ወይም በሌላ ሰው አልተመካም። ስለዚህም እግዚአብሔር ለሌላ ከፍ ላለ ጸጋ መረጠው። በሰዎች ላይ የጀመረውን ማሸነፍ በአጋንንት ላይ ደገመው። ሳኦልን ከሰዎች እጅ ብቻ ሳይሆን ከመናፍስትም እጅ የሚያድንበትን መንፈሳዊ ጉልበት ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ። ራሱ ለእግዚአብሔር መዝሙር እያዘጋጀ ስለነበረ ጎልያድን በመግደሉ ሰዎች ስለራሱ የዘመሩትን ዝማሬ አልሰማቸውም። 

ወንድሜ ከእግዚአብሔር እጅ ከዚህ የሚበልጥ ሌላ ስጦታ ስለሚጠብቅህ ያዳነህን መርምረህ ሳታውቅ የተሰጠህን አልጋ ብቻ ይዘህ አትውጣ። ከግዚአብሔር ፊት ስትወጣ የሚያገኙህ ሁሉ የሚመለከቱት መዳንህን ሳይሆን የተሸከምኸውን አልጋ ነው። ስንት ዘመን ታመህ እዚህ እንደደረስህ እነሱ አይገባቸውም። ለሕጋቸው እንጅ ለሰው የሚጨነቁ አይደሉም። ስህተቱ፥ ላንተ የሚያስብ እግዚአብሔርን ትተህ እነሱ ወዳሉበት መሄድህ ነው። ሰው አድርጎ በፈጠረህ ጊዜ ለሰውነትህ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አስማምቶ የፈጠረህ ጌታ ዛሬም አንተን ለማኖር የሚበቃ ኃይልና ፈቃድ ስላለው ሁልጊዜም ከፊቱ አትጥፋ። ሳታምን ምንም እንዲደረግልህ አትለምን። በእምነት ድል ወደማትነሣው ክብር ለመግባትም አትሞክር። 

በጸና እምነት ወስጥ ካልኖርህ፦ ክብር ቢኖርህ ከንቱ ውዳሴ ይጥልሃል። ሀብት ቢኖርህ ጥጋብ ያጠፋሃል። ዝና ቢኖርህ መታበይህ ማዕበል ሆኖ ያሰጥምሃል። ውበት ቢኖርህ ለዝሙት አሳልፎ ይሰጥሃል። ጌጠኛውን ልብስ የመልበስ ዕድል ቢያጋጥምህ ለትውዝፍት ይዳርግሃል። ወንድሜ ያለ እምነት ከሆነ በምንም ነገር እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልምና ከሁሉም ነገር በፊት እግዚአብሔር ሃይማኖትህን እንዲያጸናልህ ለምን።

“ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንደሚሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋል” ዕብ 11፥6 እንዲል!

Share your love

48 አስተያየቶች

  1. ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን። በጣም አስተማሪ ነገር ነው መምህራችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን

    • ቃለ ሕይወት ያሰማልን ሊቀ ሊቃውንት በእውነት ትልቅ መልዕክት እና አስተምሮ ነው እምነታችን ሀይላችን ሊሆን የሚገባው የሰው ልጅ ፍቅር የሳበው ሀያሉ እግዚአብሄር ነው ሰው ተሰባሪ ነው ዛሬ ተደግፈነው ነገ ራሱም ወድቆ እኛም አብረን እንወድቃለን። እግዚአብሄር አምላክ አንተ ሀይሌም ጉልበቴም ነህ ብለን ለማመንም ለመታመንም ያብቃን።

  2. በፅኑ እምነት አምነን ያድነን ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።
    የኔታ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን

  3. እውነት ነው በጣም ድንቅ ትምህርት ነው ያለ እምነት ያለ መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምንም ነገር ከንቱ ነው!!!
    ቃለ ህይወትን ያሰማልን በፀጋ በዕድሜ ያቆይልን አባታችን🙏🙏🙏

  4. በእውነት ቃለ ሕይወት ያሰማልን ረጅም የአገልግሎት ጊዜ ከጤና ጋር ያድልልን!!!

  5. በእውነት ግሩም ጽሁፍ ነው።ቃለ ህይወትን ያሰማልን መምህራችን።

  6. ቃለ ህይወትን ያሰማልን መንግስተ ሰማያት ያውርስልን ብዙ ትምርትን ነው ያተረፍኩበት

    • ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህር
      “ሰው አድርጎ በፈጠረህ ጊዜ ለሰውነትህ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አስማምቶ የፈጠረህ ጌታ ዛሬም አንተን ለማኖር የሚበቃ ኃይልና ፈቃድ ስላለው ሁልጊዜም ከፊቱ አትጥፋ።”

  7. ቃለ ህይወት ያሰማልን! በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን! አባታችን….እኛም ሰምተን የምናተርፍ የምንድን እንጂ ሰምተን የምንጠፋ አያድርገን ቸሩ መድሀኔዓለም!🙏

  8. በእውነቱ እጅግ በጣም አስተማሪ ጹሁፍ ነው። እራሴን እንድፈትሽ እና ጎዞዬን እነዳስተካክል ረድቶኛል። እና ለመምህራችን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን።

  9. ቃለ ህይወትን ያሰማልን መምህር እና

    እምነትን ለማግኘት ከኛ ምን ይጠበቃል?

  10. አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድኃለው የለው ቃል ላይ በህይወታችን የምንፈልገውን ነገር ለምነነው ከሰጠን ካደረገልን በኋላ በራሳችን ሰርተን ማምጣት እንደምንችል በራስ መተማመናችን ይጨምራል የእግዛአብሔርን ፈቃድ እንዘነጋዋለን እና እንደ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት አስተዋይ ልቦና ይሰጠን የተደረገልንን ነገር ሁሉ እንዳንረሳ በልባችን ሰሌዳ ይጣፍልን ።
    ቃለ ህይወት ያሰማልን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን ።

  11. ቃለ ህይወት ያሰማልን ክርስቶስ ገነት መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን እኛንም ባነበብነው ቃል ይለውጠን ያኑረን እግዚአብሔር አምላክ አሜን፡፡

  12. እግዚአብሔር ይስጥልን
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን
    ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን
    በዕድሜ ቀጤና ይጠብቅልን

  13. ሕያው እግዚአብሔር የሚያገለግሉበት እድሜ አብዝቶ ይስጥልን አባታችን። በጣም ጥልቅ ትምህርት ነው። መንፈሴ በጣም ደስ ነው ያላት።

  14. Эффективные стратегии арбитража трафика для повышения прибыли, для увеличения вашего дохода.
    5 причин начать заниматься арбитражем трафика прямо сейчас, без опыта в онлайн-бизнесе.
    Секреты выбора качественного трафика для успешного арбитража, чтобы минимизировать риски и максимизировать прибыль.
    Секреты эффективного таргетирования для максимального конверта, которые принесут вам стабильный доход.
    Способы заработка на арбитраже трафика без рисков и потерь, при помощи умных тактик и инновационных решений.
    арбитраж трафика топ https://traffic-arbitrage.com .

  15. Do you regularly monitor the vibration of your equipment? Vibration is a critical indicator of the health of machines and mechanisms, and neglecting it can result in severe failures.

    Using modern devices like the Balanset-1A and Balanset-4 allows for precise vibration measurements and the timely detection of issues such as bearing wear or shaft misalignment. Regular vibration monitoring helps prevent unexpected failures and extends equipment life.

    Users report significant reductions in breakdowns and downtimes after implementing regular vibration monitoring with the Balanset-1A. This not only saves money but also boosts overall productivity.

    Don’t put off taking care of your equipment. Start monitoring vibrations today with modern instruments and ensure reliable machine operation.

    Here you can read more about How do you balance a ventilation system?

  16. “Hi everyone! I’ve been thinking about drive shaft balancing, but I am not sure. On one hand, I prefer my car to run without shaking. On the other hand, it’s not cheap.

    Has anyone here had their drive shaft balanced? Is the difference significant? Does it make sense to pay for it? Thanks in advance for your thoughts and suggestions!”
    Article : drive shaft balancing

  17. На данном ресурсе представлена информация о том, как дешево приобрести игры и пополнить кошельки на платформах Steam и других популярных играх, таких как PUBG Mobile, Valorant, Genshin Impact и многих других. Пользователи могут найти выгодные предложения по покупке кода активации в разных валютах, включая гонконгские и американские доллары.

    В частности, платформа предлагает скидки на различные игры и услуги, такие как Zenless Zone Zero, Mobile Legends и DotaMall. Например, пользователи могут получить скидки до 14% на Steam USD и до 11% на Mobile Legends. Также предусмотрены услуги по пополнению кошельков Steam и покупке подарочных карт для других сервисов, таких как PSN и iTunes.

    Сайт предлагает разъяснения относительно того, что такое Steam HKD и как он может использоваться для активации кодов на аккаунтах Steam, в том числе регионах, отличных от России, США и других стран, где действуют ограничения. Пользователи могут пополнять свои аккаунты в Steam, используя коды, однако важно помнить, что они не могут активироваться на аккаунтах из стран с ограничениями, а также на аккаунтах, где используется валюта доллар США.

    Пользователи, переехавшие в Гонконг, могут сменить регион своего аккаунта Steam, пополнив его через гонконгские банковские карты. Однако рекомендуется создавать новый аккаунт с нужным регионом для избежания проблем. Если возникают трудности с активацией кода, пользователи могут обратиться в службу поддержки платформы, которая поможет решить проблему, включая замену неработающих кодов.

    Важно помнить, что при попытке активировать код на неподходящем аккаунте возврат средств будет невозможен. Поддержка осуществляется через специальную форму, а также доступны каналы в Telegram и ВКонтакте для получения актуальной информации и новостей.

    На сайте нет ограничений по сумме пополнения, однако все действия должны быть выполнены с учетом правил и рекомендаций, чтобы избежать блокировок и других проблем при использовании кодов. Присутствуют также инструкции по проверке почты в случае, если код не пришел пользователю.

    Платформа стремится обеспечить доступность и удобство для своих пользователей, предлагая широкий выбор услуг, связанных с пополнением и активацией игр в популярных онлайн-сервисах.

    пополнение steam

  18. Mysimba – Quick and Easy Weight Lass

    Mysimba is a medicine used along with diet and exercise to help manage weight in adults:

    who are obese (have a body-mass index – BMI – of 30 or more);
    who are overweight (have a BMI between 27 and 30) and have weight-related complications such as diabetes, abnormally high levels of fat in the blood, or high blood pressure.
    BMI is a measurement that indicates body weight relative to height.

    Mysimba contains the active substances naltrexone and bupropion.

    https://cutt.ly/RezL73vz

አስተያየትዎን ያስቀምጡ

Your የኢሜል አድራሻ አይታተምም። Required fields are marked *