እየኖሩ መሞት፡ እየሞቱ መኖር
ሞት በክርስትና ትርጓሜው ከእግዚብሔር ጋር በሚኖረን ቅርበትና ርቀት ይተረጐማል፡፡ ከእግዚአብሔር የሚኖረን ቅርበትና ርቀት ከነፍስ በሥጋ መለየት ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠርን ሕያዋን ስለሆነን፡፡ ነፍሳችን ከእግዚአብሔር የመገናኘት ጉልበቷን በሞት አታጣም፣ ሥጋችንም የእግዚአብሔር ጥበቃ አይለየውም፡፡ ሞት መንፈሳዊ ግንኙነትን አያቋርጥም፡፡ በሐዲስ…