ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ

የምሥጢራት ምሥጢር 

በግእዙ ምሥጢር  የምንለው በግሪክ ሚስትሪ Mystery ሲባል፤ በላቲን ደግሞ Sacrament  የሚባለው በነጠላ መጠሪያው ነው።  ምሥጢራት፣ Mysteries (Sacraments) ስንል ደግሞ በብዙ የምንጠራበት ነው። የግሪኩ ሚስቲሪዮን ከላቲኑ ሳክራመንት ጋር አቻ ቃል ነው::  ምሥጢር  ማለት ድብቅ፣ሽሽግ፣ለልብ ወዳጅ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በስተቀር የማይገለጥ ማለት…

ማንበብ ይቀጥሉየምሥጢራት ምሥጢር 

አገልግሎት ላቆም ነው

በትምህርት ቤት የማውቀው አንድ ወንድሜ ሁልጊዜ ከምንለዋወጠው የተለየ ደብዳቤ ላከልኝ፡፡ እንደተለመደው መስሎኝ ደብዳቤውን ከፍቼ እስከማየው ቸኮልሁ፡፡ ገና የመጀመሪያውን መስመር ሳነበው ደም የሚያደርቅ ንባብ ተጽፎበት አገኘሁት ደግሜ አነበብሁት፤ አገልግሎት ላቆም ነው ይላል፡፡ መጨረስ ቢያቅተኝም መጨረስ ስለነበረብኝ እየመረረኝ ጨረስሁት፡፡ የመጨረሻው መስመር ላይ…

ማንበብ ይቀጥሉአገልግሎት ላቆም ነው

የኅብረት ዝማሬ ቢበዛ ደስ ይለኛል

ከመምህር ተስፉ ግርማ ጋር በመዝሙር አገልግሎት ዙሪያ ያደረግነውን የቆየ ቃለ መጠይቅ ሁለተኛ ክፍል እነሆ::  ጃንደረባው ፦ ከመጀመሪያው ካሴት በኋላ ስንት መዝሙራትን ሠራህ? መምህር ተስፉ ግርማ ፦ በቁጥር ብዙ ናቸው ፣ ለዘማሪ ምንዳዬ ከቁጥር አንድ እስከ ሦስት ማለት ይቻላል፡፡ ‘ቸሩ ሆይ’ …

ማንበብ ይቀጥሉየኅብረት ዝማሬ ቢበዛ ደስ ይለኛል

የአምላክ እናት መሆን ትልቅ ሥራ ነው

የማርያም ጸሎት (ጸሎተ ማርያም) ሁልጊዜም ፣ በሁሉም ሥፍራ ፣ ለሁሉ የሚጸለይ ታላቅ ጸሎት ነው፡፡ ለመንገደኛው ፣ ለሚሾመው ፣ በአልጋ ላይ ላለው ሁሉ የሚጸለየው ጸሎት ይህ የማርያም ጸሎት ነው፡፡ ሹማምንት ፊት አይተው እንዳያደሉ ፣ ጉቦ ተቀብለው ፍርድ እንዳያጣምሙ የሚጸለይላቸው ጸሎት ጸሎተ…

ማንበብ ይቀጥሉየአምላክ እናት መሆን ትልቅ ሥራ ነው

ቤት ውስጥ ሆኖ መጸለይ 

የአምላኩ ምሥጋና እንዳይቋረጥበት በጎ ሥራ ሠራ አካላዊ ቃል ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለድኅነተ ሰብዕ ለድኅነተ ዓለም ሰው ሆኖ በምድር በተመላለሰበት ወቅት በተግባርም በቃልም ካስተማራቸው የክርስትና መሠረታውያን ውስጥ አንዱና ዋነኛው “ጸሎት” ነው። አድርጉ ከማለቱ በፊት አድርጎ የሚያሳይ መምህር እንደመሆኑ ጸልዩ ከማለቱ በፊት…

ማንበብ ይቀጥሉቤት ውስጥ ሆኖ መጸለይ 

ደም ላነሳት ደም ልገሳ

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ 12 ዓመት ታዳጊ የነበረችዋን የኢያኢሮስን ልጅ ከሕመሟ ለመፈወስ ሲጓዝ በመንገድ ብዙ ሕዝብ ያጨናንቀው ነበር። ከሚተራመሰው ሕዝብ የተወሰነው ተአምራት ሊያይ፤ ገሚሱ ሕብስት ሲያበረክት ጠብቆ ሊበላ፤ ሌላው መልኩን ሊያይ፤ ደግሞ ለበላይ አለቆች ያየና የሰማውን መረጃ ለማቀበል፤ የተቀረው ትምህርቱን…

ማንበብ ይቀጥሉደም ላነሳት ደም ልገሳ

የአብያተ ክርስቲያናት አርማ

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አርማዋ መስቀል ነው:: “ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሠጠሃቸው” የሚለው ቃልም የሚፈጸመው በዚሁ መንፈሳዊ አርማ ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለአስተዳደር እንዲመች ደግሞ በአህጉረ ስብከት ተከፍላ እንደምታገለግል ይታወቃል:: ለዚህ መንፈሳዊ አስተዳደርዋ ደግሞ ለእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የራሱ መታወቂያ የሆነ አርማ…

ማንበብ ይቀጥሉየአብያተ ክርስቲያናት አርማ

እግዚአብሔር ባይፈቅድ ነው

ካለፉት ቀናት መካከል አንደኛው ቀን የትምህርት ቤት ወንድሜን ለመጠየቅ የሄድሁበት ቀን ነበር። ከተገናኘን ብዙ ቀን ሆኖን ስለነበር ለእግርህ ውኃ ላሙቅልህ፣ ምግብ ይቅረብልህ አላለኝም። እንዲሁ ያለፈውን ዘመናችንን በዛሬ ዐይናችን እያየን በዛሬ ሚዛን እየመዘንን በሚያስቀው ስንስቅ በሚያስጸጽተው ስንጸጸት ቆይተን ለእንግድነቴ የሚገባው ግብዣ…

ማንበብ ይቀጥሉእግዚአብሔር ባይፈቅድ ነው

ጳውሎስና ሲላስን በመሣሪያ ያጀባቸው ሰው አልነበረም

መምህር ተስፉ ግርማ ሰባኬ ወንጌል ፣ ጸሐፊ ፣ የመዝሙር ግጥምና ዜማ ደራሲ ፣ የብዙ መንፈሳዊ ማኅበራት መሥራችና ቤተክርስቲያንን ሕይወቱን ሙሉ በቅንነት ሲያገለግል የነበረ መምህር ነው:: ዕረፍተ ነፍስ ያድልልንና መምህር ተስፉ ግርማ በነሐሴ 2013 ዓ.ም. ወደ አምላኩ ተጠርቶ በክብር ዐርፎአል::  የኢትዮጵያዊው…

ማንበብ ይቀጥሉጳውሎስና ሲላስን በመሣሪያ ያጀባቸው ሰው አልነበረም

የነፍስ ምግብ

ምንም እንኳን አንዳንድ አባትና እናቶች በይበልጥም ገዳማውያን እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ስለሚኖሩ ያለ ምግብና ውኃ ለረጅም ጊዜ መቆየት ቢችሉም፥ አካሄዳችንን ከዓለም ጋር ያደረግን እኛ ግን በተለመደው ሰዓት ካልተመገብን ረሃብና ጥም በቀላሉ ያጎሰቁለናል::  ሰውነታችን በለመደው ሥርዓት በትክክል እንዲሠራ ምግብ እና ውኃን ይሻል። ስለሆነም…

ማንበብ ይቀጥሉየነፍስ ምግብ