የሚከለክለኝ ምንድን ነው

የሚያደክሙ አጽናኞች

የኢዮብን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት ምንአልባትም የሃይስኩል ተማሪ እያለሁ ነው። ምዕራፍ ሁለትን እንደጨረስኩ ግን ከዛ በኋላ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ነው የገባኝ። በተለይ የመጨረሻው ምዕራፍ ፵፪ ላይ ስደርስ እግዚአብሔር በኢዮብ ከመናደድ ይልቅ በሦስቱ ወዳጆቹ ንግግሮች ተቆጥቶ ኢዮብን ስለእነርሱ እንዲጸልይላቸው…

ማንበብ ይቀጥሉየሚያደክሙ አጽናኞች

ከሰው ለተለዩት

የአንቀጸ ብፁዓን ተራራ፥ ወንጌል የተጀመረችበት፣ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ መምህርነቱን ለቤተ ክርስቲያን የገለጠበት ስፍራ ነው። ዘጠኙን ብፁዓን በስብከቱ የገለጣቸው በዚህ ተራራ ላይ ነው። ትምህርቱን ለመስማት በጉባኤው ለመገኘት ወደ ተራራው የወጡ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ከሁሉ ይልቅ ቀርበው ይሰሙት ነበር።…

ማንበብ ይቀጥሉከሰው ለተለዩት

ከቅዱሳን ፓትርያርኮችና ከብፁዓን አበው ጋር የተደረጉ ልዩ ልዩ ታሪካዊ የቃለ መጠይቆችን ስብስብ ክፍል ሁለት

ጥያቄ:- በግል ሕይወትዎ እመቤታችን ያደረገችልዎት ተአምር አለ? ብፁዕ አቡነ ሰላማ :- አንድ ጊዜ ወደ እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ልናከብር እንሔዳለን:: ምንጭ ዳር ተቀመጥን:: ላይ ገደል አለ እልም ያለ ገደል ነው:: ከዚያ የድንጋይ ናዳ እየተወረወረ ወደ እኛ ይመጣል:: መጥቶ ከኋላዬ ሲደርስ ዝም…

ማንበብ ይቀጥሉከቅዱሳን ፓትርያርኮችና ከብፁዓን አበው ጋር የተደረጉ ልዩ ልዩ ታሪካዊ የቃለ መጠይቆችን ስብስብ ክፍል ሁለት

ከቅዱሳን ፓትርያርኮችና ከብፁዓን አበው ጋር የተደረጉ ልዩ ልዩ ታሪካዊ የቃለ መጠይቆችን ስብስብ ክፍል አንድ ለዛሬ ተጋበዙ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ:- ለስድስት ዓመታት ተኩል ወኅኒ ቤት ታስሬ ስለቀቅ ለአንድ ዓመት ያክል በቁም እስረኝነት ከቤቴ እንዳልወጣ መንግሥት አዝዞ ነበር:: ስለዚህ ወደ ደርግ መንግሥት እንዲህ ብዬ አመለከትሁ “አሁን ተፈትቼያለሁ:: ወደነበርኩበት ሀገር ሔጄ ትምህርቴን እንድጨርስና ሀገሬን እንዳገለግል ፍቀዱልኝ:: ይህን የማትፈቅዱ…

ማንበብ ይቀጥሉከቅዱሳን ፓትርያርኮችና ከብፁዓን አበው ጋር የተደረጉ ልዩ ልዩ ታሪካዊ የቃለ መጠይቆችን ስብስብ ክፍል አንድ ለዛሬ ተጋበዙ

የቤተ ክርስቲያን ቅጥሮች

ቤተ ክርስቲያን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተች ፣ በጥምቀት ልብስ የተሸፈነች ፣ በረድኤተ መንፈስ ቅዱስ ጉልላትነት ከመዓት እሳት ፣ ከቍጣ ዶፍ የተከለለች ፣ በመስቀል ዓላማዋ የታወቀች ናት ። የተገዛችው በወልደ እግዚአብሔር ወርቀ ደም በመሆኑ ምድራዊ ዋጋ አይችላትም ። ወርቅና አልማዝም…

ማንበብ ይቀጥሉየቤተ ክርስቲያን ቅጥሮች

አመንዝራይቱን የከሰሱ አመንዝራዎች

በብዙ ጥንታውያት መዛግብት እና የሊቃውንት ትርጓሜያት ውስጥ ከዮሐ 7፡53-8፡11 ያለው የወንጌል ንባብ ተዘልሏል። ታሪኩ ተፈጽሟል አልተፈጸመም የሚለውን አኹን በዝርዝር የምናየው አይደለም። ለመጠቆም ያህል ግን ይህ የወንጌል ክፍል የሌለ መኾኑን ብዙዎች ይናገራሉ። አንዳንዱቹ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ በሌላ ቦታ ሲያደርጉት፤ አንዳንዶች…

ማንበብ ይቀጥሉአመንዝራይቱን የከሰሱ አመንዝራዎች

ልማደኛ ኃጢአተኛ የሚባል የለም

የሰውን ልጅ ተስፋ ሁልጊዜ ከሚያለመልሙ ነገሮች አንዱ እግዚአብሔር ማንንም ልማደኛ ኃጢአተኛ በሚል አለማየቱ ነው። ፊቱ ቀርበን ጌታ ሆይ አመንዝርያለሁ ወይም ሰርቄያለሁ ስንለው “ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል ዳግመኛ አትበድል፥ አሁን በሰላም ሂድ” ይለናል። በፍጹም ደስታ እንዲህ ዓይነቱንማ ጌታ እንዴት ያስቀይሙታል? ብለን የተወሰነ ጊዜ…

ማንበብ ይቀጥሉልማደኛ ኃጢአተኛ የሚባል የለም

የመጽሐፈ መነኮሳቱ አረጋዊ መንፈሳዊ ማን ነው? 

በቤተ ክርስቲያናችን “መጻሕፍተ መነኮሳት” በሚል ዐቢይ ርእስ ሥር የሚታወቁና በሦስት ሶርያዉያን አባቶች ስም የተሰየሙ መጻሕፍት አሉ። እነዚህም መጻሕፍት፦ ማር ይስሐቅ ፥ ፊልክስዩስ እና አረጋዊ መንፈሳዊ በመባል ይታወቃለ። በምንኩስና እና ገዳማዊ ሕይወት ዙሪያ የተጻፉና ከውጪ ቋንቋዎች በየጊዜው የተተረጎሙ ብዙ መጻሕፍት እያሉ…

ማንበብ ይቀጥሉየመጽሐፈ መነኮሳቱ አረጋዊ መንፈሳዊ ማን ነው? 

ጥያቄህን አታሳንሰው

በእግዚአብሔር ፊት በቆምህ ጊዜ የምታቀርበው ጥያቄ ምንድነው? “ለምኑ ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ የለመነ ሁሉ ይቀበላልና፤ የፈለገም ሁሉ ያገኛልና፤ መዝጊያ ለሚያንኳኳ ሁሉ ይከፈትለታል” ማቴ 7፥7 ብሎ በፊቱ ልመናን እንድናቀርብ ስለፈቀድልን ጸሎትና ምልጃን ማቅረብ እንችላለን። ነገር ግን ጥያቄህን አታሳንሰው፤ የቆምኸው በንጉሥ ፊት ነውና።…

ማንበብ ይቀጥሉጥያቄህን አታሳንሰው

መምህር ቀሲስ ግርማ ባቱ

“ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ነገሬ ናት:: ምንም ባደርግ ልከፍለው የማልችል የቤተ ክርስቲያን ታላቅ ውለታ አለብኝ” መምህር ቀሲስ ግርማ ባቱ  መምህር ቀሲስ ግርማ ባቱ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ መምህር ፣ ደራሲ ፣ ጸሐፊና ተመራማሪ ናቸው:: በዚህ ሰንበት በጃንደረባው ሠረገላ ላይ ይህንን ዘለግ ያለ…

ማንበብ ይቀጥሉመምህር ቀሲስ ግርማ ባቱ