ሙሉዓለም ጌታቸው

ሙሉዓለም ጌታቸው

የቶልስቶይ ወንጀለኞች

የዛሬው ጹሁፍ በውሳኔ አሰጣጥ ጉዳይ እና በሕይወት ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎችን ስንወስን የሚገጥሙን የሥነ ልቡና ዝንፈቶችን (cognitive dissonance) ይዳስሳል። ስለ ውሳኔ ስናስብ ስለ ራሳችን ማሰብ ግድ ይለናል። ምክንያቱም ለራሳችን ያለን ግምት ነው በውሳኔ አሠጣጥ ሒደታችን ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድረው። ስለራሳችን ያለን…

በትሕትና ማደግ

ስለብዙ ነገር መጻፍ ይቻላል፤ ስለትሕትና ግን ለመናገር እና ለመጻፍ በኛ ደረጃ ላለ ድፍረት (ጥቂት ትዕቢት) ይፈልጋል። ትሑት ልትሆን ትችላለህ ግን ትሑት እንደሆንክ ባሰብክ ሰዓት ትህትናህን አጥተኸዋል። ትህትናን ከባድ የሚያደርገው ያ ነው። ትሁት እንደሆንክ እያሰብክ ትሁት መሆን አትችልም። ትህትና በመሆን ብቻ…

ከማን ጋር እንደምታወራ አታውቅም

በሥጋ ማርያም ተገልጦ፥ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በአይሁድ ምድር ሲመላለስ “አምላካቸውን ያዩት ሰዎች እንዴት ታድለዋል?” የሚል ነገር አንዳንዴ ውል ይልብኛል:: (ይሄ ዘወትር የምንደነቅበት ነበር መሆን ያለበት)።  ተመልከቱ ቅዱስ ሉቃስ  “እንደልማዱ በሰንበት ወደ ምኩራብ ገባ” ይለናል። (ሉቃ 4፥26) በዕለተ ሰንበት…

ከቤተ ክርስቲያን የሚያሸሹን ሰዎች 

ብዙዎቻችን ከቤተክርስቲያን የምንርቅበትን ወይም ከክርስትና የወጣንበትን ምክንያት ስንገልጽ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ አገልጋዮችን እንደምክንያት እንጠቅሳለን። የእናንተን አላውቅም እኔ ግን እንደዛ እል ነበር። እንደሚመስለኝ ብዙ ሰዎች ከጳጳሳቱ ጀምሮ እስከታች እስካሉት ዲያቆናት ማንነት እየጠቀሱ ምን ያህል አስመሳዮች እና ኃጢአተኞች እንደሆኑ በመናገር፣ ሁሉም…

የሚያደክሙ አጽናኞች

የኢዮብን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት ምንአልባትም የሃይስኩል ተማሪ እያለሁ ነው። ምዕራፍ ሁለትን እንደጨረስኩ ግን ከዛ በኋላ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ነው የገባኝ። በተለይ የመጨረሻው ምዕራፍ ፵፪ ላይ ስደርስ እግዚአብሔር በኢዮብ ከመናደድ ይልቅ በሦስቱ ወዳጆቹ ንግግሮች ተቆጥቶ ኢዮብን ስለእነርሱ እንዲጸልይላቸው…

ንባብ ግብ አይደለም

ስለ ሲ ኤስ ሉዊስ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መጽሐፍ እንደጀመርኩ የእውቀት እና የመንፈሳዊ ሕይወት ዓርአያዬ የሆነ የመንፈስ ታላቅ ወንድሜ ሲ ኤስ ሉዊስ ለቅዱስ አትናቲዎስ ነገረ ሥጋዌ መጽሐፍ ትርጉም የጻፈውን መግቢያ እንዳነበበው እና በሉዊስ እንደተደመመ ነገረኝ። እኔም ወዲያው ያን መግቢያ ፈልጌ ማንበብ…