ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

አቤቱ የሚያሰቃዩኝ ምንኛ በዙ?

ብዙዎች በእኔ ላይ ቆሙ፡፡ ብዙዎች ሰውነቴን አምላክሽ አያድንሽም አሏት፡፡ አንተ ግን አቤቱ መጠጊያዬ ነህ፡፡ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ (መዝ. 3፡1) ነቢዩ ዳዊት ክፉ ቀን ቢገጥመው የጸለየው ጸሎት ነው፡፡ መራራ ቀናት ሀገር ያስለቅቃሉ፡፡ ከዙፋን ያወርዳሉ፡፡ ማቅ ያስለብሳሉ፡፡ ለብቻ…

የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ጸሎት

አቤቱ “በጎውን ነገር ማን ያሳየናል?” የምንልበት ዘመን አይደለም፤ እንኳን በእኛ ዘንድ ይቅርና ወንጌል በአሕዛብ ዘንድ ሳይቀር የተሰበከበት ዘመን ነውና። ነገር ግን የተሰበከውን ቃል በልቤ አኑሬ ሕይወቴን ሳልለውጥበት ብዙ ዘመናትና ዓመታት አለፉ። ቃልህን ሰምቶ አለማድረግ በአንተ መዘባበት መሆኑን አውቃለሁ፤ ቃልህን የምሰማ…

አገልግሎት ላቆም ነው

በትምህርት ቤት የማውቀው አንድ ወንድሜ ሁልጊዜ ከምንለዋወጠው የተለየ ደብዳቤ ላከልኝ፡፡ እንደተለመደው መስሎኝ ደብዳቤውን ከፍቼ እስከማየው ቸኮልሁ፡፡ ገና የመጀመሪያውን መስመር ሳነበው ደም የሚያደርቅ ንባብ ተጽፎበት አገኘሁት ደግሜ አነበብሁት፤ አገልግሎት ላቆም ነው ይላል፡፡ መጨረስ ቢያቅተኝም መጨረስ ስለነበረብኝ እየመረረኝ ጨረስሁት፡፡ የመጨረሻው መስመር ላይ…

እግዚአብሔር ባይፈቅድ ነው

ካለፉት ቀናት መካከል አንደኛው ቀን የትምህርት ቤት ወንድሜን ለመጠየቅ የሄድሁበት ቀን ነበር። ከተገናኘን ብዙ ቀን ሆኖን ስለነበር ለእግርህ ውኃ ላሙቅልህ፣ ምግብ ይቅረብልህ አላለኝም። እንዲሁ ያለፈውን ዘመናችንን በዛሬ ዐይናችን እያየን በዛሬ ሚዛን እየመዘንን በሚያስቀው ስንስቅ በሚያስጸጽተው ስንጸጸት ቆይተን ለእንግድነቴ የሚገባው ግብዣ…

በፈተና ላሉት

ይሄ ፈተና ከምን መጣ? ፈተናው ከእኛ ጋር ካሉት ይልቅ በእኛ ላይ ለምን በዛ? ምንጭ የሌለው ፈተና ባይኖርም ምንጩን ሳናውቀው በመጣ ፈተና ነፍሳችን ደከመች። ሰውነታችን ኑሮን ሰለቸች። ፈተናው አስመርሮናል፤ መከራው ከብዶናል ነገር ግን የፈተናውን ምክንያት ሳናውቅና ሳንመረምር ከፈተና ወደ ፈተና ስንሸጋገር…

ተመየጢ ተመየጢ

“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ ተመለሽ” መኃ 7፥1  በኖኅ መርከብ ውስጥ ሆኖ ዐይኖቹ አሻግሮ ማየት የማይፈልግ ማን አለ? ከዚያ ሁሉ ጥፋት በኋላ ምድርን መልሶ ማየት ያጓጓል። ለዐርባ ቀናት ከሰማይ የወረደውና ከምድር የገነፈለው ትኩስ ውኃ የተራሮችን ራስ ሳይቀር…

ለመጽደቅ ከሆነ በቂ ነው

አንዳንድ ቀን አለ አንጀት የሚያላውስ ፤ የለቅሶ ስሜትን የሚቀሰቅስ ችግር በሰዎች ላይ ሲደርስ የምንገጣጠምበት፤ ታዲያ በዚህ ሰዓት ምነው “እግዚአብሔር ሀብታም ቢያደርገኝና በሰጠኋቸው” ብለን እንመኛለን። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የማይገባ ምኞት ነው ይለዋል። እግዚአብሔር ቢያስፈልግ ኖሮ ካንተ ቀድሞ ይህንን ሳያስብ የሚቀር…

ከሰው ለተለዩት

የአንቀጸ ብፁዓን ተራራ፥ ወንጌል የተጀመረችበት፣ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ መምህርነቱን ለቤተ ክርስቲያን የገለጠበት ስፍራ ነው። ዘጠኙን ብፁዓን በስብከቱ የገለጣቸው በዚህ ተራራ ላይ ነው። ትምህርቱን ለመስማት በጉባኤው ለመገኘት ወደ ተራራው የወጡ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ከሁሉ ይልቅ ቀርበው ይሰሙት ነበር።…

ጥያቄህን አታሳንሰው

በእግዚአብሔር ፊት በቆምህ ጊዜ የምታቀርበው ጥያቄ ምንድነው? “ለምኑ ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ የለመነ ሁሉ ይቀበላልና፤ የፈለገም ሁሉ ያገኛልና፤ መዝጊያ ለሚያንኳኳ ሁሉ ይከፈትለታል” ማቴ 7፥7 ብሎ በፊቱ ልመናን እንድናቀርብ ስለፈቀድልን ጸሎትና ምልጃን ማቅረብ እንችላለን። ነገር ግን ጥያቄህን አታሳንሰው፤ የቆምኸው በንጉሥ ፊት ነውና።…

ይህ ሁሉ ይጨመርላችኋል

የጌታን ቃል ማን ያምነዋል? የመልዕክተኞቹን ምስክርነትስ ማን በሚገባ ይቀበለዋል? ለዚህም ነው ከነቢያት እስከ ሐዋርያት ድረስ “እግዚኦ መኑ የአምነነ ስምዐነ፤ አቤቱ ብንናገርስ ምስክርነታችንን ማን ያምነናል?” እያሉ የተናገሩት። ከነቢያት ኢሳይያስ ከሐዋርያት ዮሐንስና ጳውሎስ ይህንን ቃል ጠቅሰውታል። ኢሳ  53፥1፣ ዮሐ 12፥38፣ ሮሜ 10፥16…