ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

ከእምነት በፊት መዳን

የተፈጠርነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ሰው ሆነን ወደ ምድር የመጣንበትን ዘመን፣ የተገኘነበትን ምድር፣ የወጣንበትን ማኅበረ ሰብእ እና ሌሎችንም ጉዳዮች የመረጠ እርሱ እግዚአብሔር ነው። አዳም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ በራሱ ምርጫ ራሱን ያስገኘ ማን አለ? አጭር ወይም ረዥም፣ ቀጭን ወይም ወፍራም፣ ነጭ ወይም…

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ | ክፍል ፫

ክፍል ፫ ፐሊካን {ጳልቃን}   ፍቅር ሲሰጧቸው ፍቅር መመለስ የማይቻላቸው ገላግልት ያሏት ያልታደለች ወፍ ናት − ፔሊከን። የእኛ መምህራን በትርጓሜአቸው ጳልቃን ብለዋታል። ጫጩቶቿን እጅግ አድርጋ ትወዳለች፣ አብዝታም ትታቀፋቸዋለች። እነሱ ግን ሲበዛ አስቸጋሪዎች ናቸው። ገና ክንፍ ማውጣት ሲጀምሩ ጀምሮ ፊቷን በክንፋቸው…

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ | ክፍል ፪

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ ክፍል ፪ ወጥመድ የሌለበት የሕይወት መንገድ ያጋጠመው ከፍጡራን መካከል ማንም የለም። በመላእክት ዘንድ ሳጥናኤል ነበረ። በሰዎችም ዘንድ የእድሜ ልክ ጠላትነት ካለብን ከሰይጣን ዘንድ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይታጠፍ ተዘርግቶ የሚኖር ወጥመድ አለ። ለዚህ ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ወጥመድ በአንተ…

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ

ክፍል ፩ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያው ጉባኤ ካስተማረን ትምህርት አንዱ ይህ ነው − የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ አለ። የሰው ልጅ በክርስትና የኑሮ ለውጥ ማድረግ ይገባዋል። ክርስቲያን ስትሆን በሕይወትህ ውስጥ ልትሠራው የሚገባህን ብቻ ሠርተህ ልትሠራው የማትችለውን…

ተሰናባቹ ሽማግሌ

በሕይወት መጨረሻ፤ በዘመን ፍጻሜ ላይ የተመኙትን ማግኘት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። የሰው ልጅ መንገድ በፍለጋ የተሞላ ነው። አንዳንዱ የተመኘውን አግኝቶ ደስ ብሎት ወደ መቃብር ይወርዳል፤ አንዳንዱም ወደ ተመኘው ዓለም ሲገሰግስ ሞት ያደናቅፈውና በምኞቱ ሳለ ነፍሱን ይነጠቃል።  በጌታ የልደት ዘመን…

ከሞትህ አይጣሉህም!

በክርስትና ትምህርት ሞት የሕይወት ፍጻሜ ሳይሆን የምድራዊ ሕይወት መጨረሻ፤ የሰማያዊ ሕይወት መጀመሪያ ነው። ክርስቲያኖች በሞት ምክንያት የሚመጣ ኃዘን የማይጸናባቸውም ስለዚህ ነው። ከሞት በኋላ ለማንም በምድር ላይ ዕድል ፈንታ የለውም። በእርግጥ ይህ የሚሆነው በዓለም ዘንድ ነው እንጅ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ግን…

ሴምና ያፌት

ምድር ከጥፋት ውኃ መድረቅ በኋላ በኖኅ መርከብ ውስጥ ከነበሩ እንስሳትና አራዊት በቀር ሌላ አንዳች ፍጥረት አልነበረባትም። በምድር ላይ የሚርመሰመሰውን ሥጋ ለባሽ ፍጥረት ሁሉ ለጥፋት የዘነበው ውኃ ሙልጭ አድርጎ ደምስሶታል። ኖኅ ከመርከብ ሲወጣ ምድርን በዝሙታቸው ያበላሿት የቃኤል ልጆች በከተሞቻቸው አልነበሩም። ቅዱስ…

የኢየሱስ እናት በዚያ ነበረች

አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና” ከገዳም ከተመለሰ፣ ጉባኤ ሠርቶ ማስተማር ከጀመረ እነሆ ሦስተኛ ቀን ሆነው። በሦስተኛው ቀንም በታናሿ መንደር በቃና ሠርግ ተደረገ። ይህ ሠርግ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይነት የተገለጠበት ሠርግ ነው። ለሐዋርያት ሰውነቱ ከአምላክነቱ፣ አምላክነቱ ከሰውነቱ…

ክርስቶስ ተወልዶላችኋል

በእውነት ይህንን የሚመስል አዋጅ ሰምተን እናውቃለን? ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን የምሥራችን ያስከተለ ልደትን ማን ተወለደ? በመላው ዓለም ለሚገኙ የሰው ልጆች ሁሉ “ተወልዶላችኋል” ተብሎ ዜና ልደቱ የተነገረለትስ ማን አለ? ሔዋን በምድር ላይ መውለድን በጀመረች ጊዜ ይህ ዐዋጅ አልነበረም። ሣራም በእርጅናዋ ወራት ፀንሳ…

የአእላፋት ዝማሬ – የቅዱስ ኤፍሬም ጥሪ

ቅዱስ ኤፍሬም ቤተ ክርስቲያንን በድርሳን ካስጌጡ ሊቃውንት መካከል የሚመደብ ሊቅ ነው። አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሊቃውንትና መነኮሳትንም ያገኘችበት ዘመን ነው። በዘመነ ሰማዕታት የነበረው የቤተ ክርስቲያን ተጋድሎ ያፈራቸው ሊቃውንትና መነኮሳት ናቸው። ከዚያ በኋላ ጉባኤ ቤቶች ሰፉ፤ ገዳማት ተመሠረቱ።…