የበረኸኛው መልስ
ቆዳ አገልድሞ ፀጉሩን አንጨፍሮ በሄኖን ሸለቆ ወደሚጮኸው ሰው ሰው የሚያየውን ልይ ብዬ መጣሁ። የገባውን በቃል ያልገባውን በውኃ እያጠመቀ ይሸኛል። ደግሞ ጠያቂዎች መልሱን የሚፈሩትን ጥያቄዎች ይጠይቁታል፡፡ ይህ የሰው ጠባይ ይደንቃል። ጥያቄ ሲፈጠርበት መልሱን ይፈራል፤ የማይኖረውን መልስ ለመስማት ይጠይቃል። ሁሉንም ግን አያቆምም፤…
ቆዳ አገልድሞ ፀጉሩን አንጨፍሮ በሄኖን ሸለቆ ወደሚጮኸው ሰው ሰው የሚያየውን ልይ ብዬ መጣሁ። የገባውን በቃል ያልገባውን በውኃ እያጠመቀ ይሸኛል። ደግሞ ጠያቂዎች መልሱን የሚፈሩትን ጥያቄዎች ይጠይቁታል፡፡ ይህ የሰው ጠባይ ይደንቃል። ጥያቄ ሲፈጠርበት መልሱን ይፈራል፤ የማይኖረውን መልስ ለመስማት ይጠይቃል። ሁሉንም ግን አያቆምም፤…
ጸሎት እየጸለይን: ለጸሎታችን መልስ ሳናገኝ ስንቀር ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋል። አንዳንድ ጊዜ ዝምታውም መልስ እንደሆነ ለማይረዳ ሰው ወይም ደግሞ ፈቃድህ ይሁን ብሎ ለማይጸልይ ሰው የጸሎት መልስ ጊዜው ሲረዝም ተስፋ ወደ መቁረጥ ውስጥ ያስገባል። ማለትም “ፈቃድህ ይሁን” የሚለውን መስመር አባታች ሆይ የሚለው…
የሰውን ልጅ ተስፋ ሁልጊዜ ከሚያለመልሙ ነገሮች አንዱ እግዚአብሔር ማንንም ልማደኛ ኃጢአተኛ በሚል አለማየቱ ነው። ፊቱ ቀርበን ጌታ ሆይ አመንዝርያለሁ ወይም ሰርቄያለሁ ስንለው “ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል ዳግመኛ አትበድል፥ አሁን በሰላም ሂድ” ይለናል። በፍጹም ደስታ እንዲህ ዓይነቱንማ ጌታ እንዴት ያስቀይሙታል? ብለን የተወሰነ ጊዜ…
ከጌታ እግዚአብሔር ጋር የተዋሐዶ ሕይወትን መኖር የሚፈልግ ስብከት ከመስማት፣ መጽሐፍ ቅዱስና አዋልድ መጻሕፍትን ከማንበብ በማያንስ ደረጃ ማንበብ ያለበት ሌላ ትልቅ መጽሐፍ አለ፤ ፍጥረት! የተሰጣቸው ግዕዛን ከጌታ እግዚአብሔር ጋር ደረጃው ከፍ ያለ ግንኙነት ላጎናፀፋቸው መላእክትና ሰው ጌታ እግዚአብሔር በፍጥረት ጭምር ሀልዎቱንና…
ከእርጋታውና እኔንም እንደ አዋቂ ከመቁጠሩ ሳይወጣ “ስለ ቀደሙት ሰዎች ሕይወት ሁሉን የመስማት ዕድል አግኝተሃል? የኖረውንስ ልማድ እንዳለ የመቀበል ግዴታ ተጥሎብሃል? አንተን ፈጣሪ ሲፈጥርህ መልክህ፣ አሻራህ፣ ድምፅህ ከአንተ በፊት የነበሩትን አይመስልም። ከአንተም በኋላ አንተን የሚመስል አይመጣም። ሌሎችን በማይመስል መልክህ መኖር ካልተቸገርህ…
በእውነታ ላይ የተመሠረተ ምናባዊ ጽሑፍ በቅርብ በቅዱስ ጋብቻ አንድ ከሆኑ ጥንዶች ጋር ስለ ክርስትና ሕይወታቸው አባታችንን ለማወያየት ፈልገው በቤታቸው ተገናኘን፡፡ በውይይታችን ከተነሡት በርካታ ጉዳዮች የዘመኑን የክርስትና ሕይወት አጉልቶ የሚያሳዩ ሁለት ነጥቦችን እነሆ፡- የመጀመሪያው ከእንግዶቹ የተነሣው ሐሳብ “ከአንዳንድ ወንድምና እኅቶች ጋር…