በሕይወት መጨረሻ፤ በዘመን ፍጻሜ ላይ የተመኙትን ማግኘት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። የሰው ልጅ መንገድ በፍለጋ የተሞላ ነው። አንዳንዱ የተመኘውን አግኝቶ ደስ ብሎት ወደ መቃብር ይወርዳል፤ አንዳንዱም ወደ ተመኘው ዓለም ሲገሰግስ ሞት ያደናቅፈውና በምኞቱ ሳለ ነፍሱን ይነጠቃል። 

በጌታ የልደት ዘመን ከነበሩትና በቅዱስ ወንጌል ስማቸው ከተመዘገቡት ሰዎች መካከል ድንቅ ነገር የተመኘ ምኞቱም የተከናወነችለት ስምዖን የሚባል ሰው አለ። በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ ሰዎች ስላሉ ከእነዚያ ለመለየት ስምዖን አረጋዊ ተብሎ ይጠራል። ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሲመላለስ በነበረ ጊዜ ብዙ ስምዖኖች አግኝተውታል። ለምጻሙ ስምዖን ማቴ 26፥6፣ ፈሪሳዊው ስምዖን ሉቃ 7፥40፣ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ዮሐ 1፥42፣ እና ሌሎችም ማቴ 10፥4። 

እነዚህ ሁሉም ስማቸው እንጅ ግብራቸው የተለያየ ነው። እነዚህ ሁሉም አንድ የሚያመሳስል ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ እሱም ጌታን ማየታቸው ነው። ሕይወት ግዙፍ አካል ኖሯት በሰዎች መካከል ስትመላለስ ማየት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገርም አይደል? በሰማይ ላይ የሚታዩት ፀሐይ እና ጨረቃ ሥጋ ለብሰው ብታገኟቸው አትገረሙም? ሚካኤልና ገብርኤል ቤታችሁ መጥተው እንግዳ ቢሆኑላችሁስ ዜናውን ለሰው ሁሉ በደስታ አታወሩም? መልሳችሁ አዎ ከሆነ ለእነዚህ ሰዎች ከዚህ የሚበልጥ ነገር እንደተደረገላቸው አስተውሉ። 

መላእክትን የሾመ፣ ፀሐይና ጨረቃን በማያረጅ ብርሃን የሸለመ እግዚአብሔር በሥጋ በመካከላቸው ሲመላለስ አዩት። ከዚህ የሚበልጥ ምን አለ? 

ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ በሕይወት አጋጣሚ እንዲህ ያለውን መልካም ነገር ተቀብለዋል እንጅ አስበውበት የተቀበሉት ስጦታ አይደለም። አንዳንዶቹ ግን የልባቸው ምኞት ይህች ነበረች − ክርስቶስን ማየት። ስምዖን አረጋዊ ረዥም ዓመታትን በምድር ላይ የዘገየው ክርስቶስን ጥበቃ ነው። በዘመኑ ብዙ ነገር ሲከናወን አይቷል፤ ገናናው የጽርዕ መንግሥት ዓለምን አሸንፎ ሲገዛ አይቷል። የጽርዕ መንግሥት ወድቆ የሮማ መንግሥት ሲቋቋምም ነበረ። 

ከእስክንድር እስከ ቄሣር ብዙ ነገሮችን ተመልክቷል። የእሱ ፍለጋ ግን ገና አልተቋጨም። ስንቱን አየው? እስራኤል ቀድሞ ለባቢሎን ሲሰግዱ፣ በኋላም ለግሪክ ሲያጎበድዱ፣ ቀጠሉና ለሮም ሲያደገድጉ አይቷል እሱ ግን ከቆመበት የሃይማኖት መድረክ አልወረደም። 

ነፍሱ የቃተተችለት ፍለጋ ገና አልተጠናቀቀም። ዘመን ሲለወጥ ሀሳቡን አልለወጠም። ንጉሥ ሲቀየር ተስፋው አልተቀየረም። ግሪክ ወድቃ ሮም ስትተካ የእሱ ተስፋ አሁንም ባለበት ነው። የእግዚአብሔርን መምጣት ተስፋ ያደርጋል። የመጡትም ሆነ ያለፉት ተሰፋውን አልፈጸሙለትምና ተስፋውን የሚፈጽምለት ይፈልጋል። የተሾሙትም ሆነ የተሻሩት ከተስፋው ፈቀቅ አላደረጉትም። አሁንም ክርስቶስን ፍለጋ። እሱ የሚያርፈው የወገኖቹን የእስራኤልን የመጽናናት ዘመን ሲመጣ ሲያይ ብቻ ነው። መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ፍለጋ ይህ ነውና። 

ዛሬ ለዚያ ሰው ምኞቱ ትፈጸምለት ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ በመንፈስ ወጣ። ሊያየው የተመኘው ክርስቶስም በዚያ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ የሚገባበት ቀን ነበረ። አገኘው፤ አየው፤ አቀፈው። 

ሰምታችሁኛል ወገኖቼ? ስምዖን የእስራኤልን መድኃኒት አቀፈው እያልኋችሁ እኮ ነው። ዳንኤል ከረዥም ተራራ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ሲወርድ ያየውን ድንጋይ ስምዖን በዐይኖቹ አየው ዳን 2፥34። ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ከሐመልማል ጋር ተዋሕዶ ያየውን የእሳት ነበልባል በክንዶቹ ታቀፈው ዘፀ 3፥2። አዳም በገነት መካከል ሲመላለስ ሰምቶት የፈራውን ስምዖን ሳይፈራ ዳሰሰው ዘፍ 3፥10። 

እንደ አዳም የሚናዘዝ፤ እንደ ቃኤል የሚቅበዘበዝ ሰው አልነበረምና ተስፋ ያደረገውን ክርስቶስን በዕቅፉ ይዞ ምስጋናውን ቀጠለ። ቅዱስ ወንጌል እንደ ተናገረ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ። “ጌታ ሆይ እንደ ቃልህ ዛሬ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ዓይኖቼ በሰው ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና” ሉቃ 2፥29−32 እያለ ምስጋናውንም ልመናውንም አቀረበ። የአንዳንድ ሰው ታሪክ በአንድ ቀን ተጀምሮ በአንድ ቀን የሚፈጸም ነው። 

አንዳንዱ ሰው አንድ ቀን ብቻ ኖሮ የሚሞት ነው። ይህች ቀን ለዚህ ሰው እንዲሁ ናት። ከዚህች ቀን አስቀድሞም ሆነ በኋላ በወንጌል ለመጻ’ፍ የሚያበቃ ታሪክ የለውም። ከኖረባቸው ቀናት መካከል ያለዚህች ቀን የኖረበት ቀን የለም። ሊሎቹ ቀናት ይህችን ቀን ሲፈልግ የቆየባቸው ቀናት ስለሆኑ አይቆጠሩም። ዕድሜው አንድ ቀን ናት − ግን በቂ ናት። ለዚህም ነው “ዛሬ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ” ብሎ መለመኑ። 

ሽማግሌው ስምዖን ስንብት ለመነ። ከሦስት መቶ ዓመት በላይ የቆየባትን ዓለም ሊሰናበታት ለመነ። ወዳጆቼን ልሰናበት፣ ሀብቴን ንብረቴን ላስተናብር አላለም። እንደ ዮፍታሔ ልጅ ለድንግልናው፣ እንደ ዳዊትም ለሽምግልናው ዕድሜ አልለመነም መሳ 11፥37፣ መዝ 102፥24። “አሰናብተኝ” አለ። 

ምን ያደርጋል ዕድሜ፣ ምን ሊያደርግ መቆየት ሰው የሕይወቱን ግብ ካደረሰ። እነዚያ ሁሉ ዘመናት ከዚህች ቀን አይበልጡም። በእነዚያ ሁሉ ዓመታት ያየው ነገር ሁሉ ዛሬ ያየውን አያኽሉም። ይሄ ሰው አንድ ዘመን ላይ በገናናው ንጉሥ በበጥሊሞስ ቤተ መንግሥት በጥበባቸው ከተመረጡት ሰዎች መካከል ነበረ። ይሄ ሰው በምቹ የቤተ መንግሥት ሰገነቶች የተመላለሰባቸው ቀናት በሕይወቱ ውስጥ አልፈዋል። እንዲህ ያለ የስንብት ልመና ሲያቀርብ አልተሰማም። በንጉሥ ድንኳን ማደር፣ ከልዑላን ጋር መኖር እንደዚህች ቀን ያለ ደስታን እንደማያስገኝ ያውቀው ነበርና። 

ዛሬ ግን ከዚህ የሚበልጥ ቀን እንደማይመጣ ያውቃልና አሰናብተኝ ብሎ ለመነ። ከዚህ በኋላ የሚመጣውን የሔሮድስን ቀን ሳያይ ሊሞት ተመኘ። 

የገሊላ አውራጃ በደም የምትሞላበት በእናቶቻቸው ዕቅፍ ያሉ ሕጻናት አንገት የሚቀላበት ዘመን ሳይደርስ መሞት አማረው። አስጨናቂው ዘመን ሳይመጣ “ድምፅ በራማ ተሰማ ለቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች መጽናናትም አልወደደችም የሉምና” የተባለው ቃል ሳይፈጸም መሄድ ፈለገ ማቴ 2፥18። የሚመጡት ዐመታት የኢየሩሳሌም ቆነጃጅት በአደባባይ ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱባቸው ዘመናት ናቸው። የጽዮን ቆነጃጅት በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ሙሾ ያወጣሉ የሚሰማቸው ግን የለም፤ ከዚህ የሙሾ ጉባኤ መካፈል አልፈለገምና ዛሬ አሰናብተኝ አለ። 

በሚመጡት ቀናት በከተማ ሁከት ያስነሣውን በርባንን አስፈትተው ከሞት ማሠሪያ የፈታቸውን ኢየሱስን ስቀልልን የሚል ትውልድ ይነሣል፤ ይህን ክፉ ትውልድ ሳያይ ሊሞት ወደደ። እንዴት በአንድ ዘመን ከቤተ ክህነትም ከቤተ መንግሥትም ፍርድ ጎደለ፣ ድሀ ተበደለ የሚል ይጠፋል? ከዚህ ቀንስ አታድርሰኝ ብሎ በጌታ ፊት ማንም ያላቀረበውን ልመና አቀረበ − “ዛሬ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ”።

ክርስቶሳውያን ወገኖቼ ሆይ! ከሕይወት የሚሻል ሞት አለ። ነቢዩ ዳዊት “ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላል” መዝ 63፥3 ያለው እንዲህ ያለውን ሞት ነው። ከመኖርም የሚበልጥ አለመኖር አለ። ይልቁንም በሰማዩ መንግሥት ለሹመት የምታበቃንን ቀን ካገኘናት ከዚያ በኋላ ያለው ቀን አይጠቅመንም። ወደ እግዚአብሔር የተመለስንበት፣ ንስሐ የገባንበት፣ ንስሐ በመግባታችን በሰማይ መላእክት ዘንድ ሰለኛ ታላቅ ደስታ የተደረገበት፣ ሥጋውን ደሙን የተቀበልንበት ያ ቀን ለእኛ የአረጋዊው ስምዖነ ቀን ነው። ከኖርንበት ዓለም ለመሰናበት የመልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረብ ያለብን በዚህ ቀን ነው። ይህን ቀን ከቀናቶቻችሁ መካከል ፈልጉት።

ለጠፉ በጎች ግን ከዛሬ ነገ ይሻላቸዋልና “ዛሬ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ” ብለው ስንብት ሊጠይቁ አይገባም። ዓይኖቻቸው ማዳኑን ማየት ያለባቸው በምድር ሳሉ እንጅ በሰማይ አይደለም። የእግዚአብሔርን ምሕረት በምድር እንጅ በሰማይ አናየውም። ይቅርታውን በምድር እንጅ በሰማይ አናገኘውም። ከካህናት እጅ ያልተቀበልናትን የእግዚአብሔር መንግሥት ከሰማይ መላእክት እጅ የምንቀበል የሚመስለው ካለ ተሳስቷል። መንግሥተ ሰማያትን በምድር ሳለ ያልተቀበላት በሰማይ አያገኛትም። በምድር ሳለ የመምህራንን ቃል የሚንቅ ሰው በሰማይ ያለ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደማይሰማ ጌታ በቅዱስ ወንጌል አስጠንቅቋል ሉቃ 10፥16 የወጣንያን ጸሎት “አቤቱ በእኩሌታ ዘመኔ አትውሰደኝ” መዝ 102፥24 ነው። የፍጹማን ጸሎት ግን ይህ ነው “ጌታ ሆይ እንደ ቃልህ ዛሬ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ” ሉቃ 2፥29

Share your love

66 አስተያየቶች

  1. ዛሬ በርትቼ አነበብኩ! ተስፋ እንዳትቆርጡብን እና መጻፍ እንዳታቆሙ። እግዚያብሔር ይስጥልን!

  2. ” ከመኖርም የሚበልጥ አለመኖር አለ። ”
    ሊቀ ሊቃውንት ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  3. ለመምህራችን ቃለ-ሕይወት ያሰማልን፤ የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክልን/ያርዝምልን፡፡

  4. ሕይወት ግዙፍ አካል ኖሯት በሰዎች መካከል ስትመላለስ ማየት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገርም አይደል?

  5. መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን ፣ በቤቱ ያፅናልን ፣የአገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክልን።

  6. “ከመኖርም የሚሻል አለመኖር አለ” ሊቀ ሊቃውንት ሰምዓ ኮነ። ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መምህር፣ አስበ መምህራንን ያድልልን🙏🌺

  7. በየሳምንቱ እየጠበኩ ነው የማነበው፡፡ ለነፍስ እረፍትን የሚሰጥ ነዉ፡፡ እግዚአብሄር ይስጥልን መምህር፡፡

  8. እንደነዚህ አይነት መጻሕፍት በሊቃውንቶቻችን እይታና በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምሮት ሲወጡ ማንም ባልተረዳውና ባልተማረው ለመተርጎምም ከመሞከር እንዲታቀብ ይረዱታል

  9. እንደነዚህ አይነት መጻሕፍት በሊቃውንቶቻችን እይታና በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምሮት ሲወጡ ማንም ባልተረዳውና ባልተማረው ለመተርጎምም ከመሞከር እንዲታቀብ ይረዱታል ቃለሕይወትን ያሰማልን መምሕራኖቻችንን ይጠብቅልን

  10. Высококвалифицированные мастера и современное оборудование
    Автосервис в Москве [url=https://www.tokyogarage.ru]https://www.tokyogarage.ru[/url].

  11. ቃለ ህይወት ያሰማልን ደስ በሚል አገላለጽ ሆኖ እራሳችንን የምንጠይቅበት ነው

  12. “ከመኖር የሚበልጥ አለመኖር አለ”
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን
    በየጊዜው እንዲህ እያደረጋችሁ መግቡን።

  13. ለ ህይወት የሚሆን ቃል አሰምታቹናልና …ቃለ ህይወት ያሰማልን !

  14. Какие еще существуют показания для биоревитализации? Показания включают лечение фотостарения, улучшение цвета лица и коррекцию мелких морщин
    аквашайн биоревитализация http://biorevitalizacia.com/ .

  15. Особенности индивидуального заказа перетяжки салона автомобиля в Москве.
    Какие стили и дизайны доступны для перетяжки салона автомобиля в Москве?
    Перетяжка салона http://poshiv-avtosalona.ru/ .

  16. Каждый год в середине сентября проводится Тюменский инновационный форум «НЕФТЬГАЗТЭК».
    Форум посвящен устройству мнтодов инновационного продвижения секторов топливно-энергетического комплекса, рассмотрению а также поиску заключений, образованию наилучших условий для расчета инновационных проектов. Ежегодный тюменский форум представляетсобой авторитетной дискуссионной площадкой по продвижению нефтегазовой отрасли в Российской Федерации, имеет большой авторитет и актуальность, созвучен корпоративной стратегии продвижения инновационного направления в Российской Федерации
    https://neftgaztek.ru/

  17. Какие аспекты важны при строительном аудите в Москве, которые важно учесть.
    Аудит строительного контроля помогает выявить несоответствия и улучшить процесс управления проектами. Аудит строительного контроля помогает выявить несоответствия и улучшить процесс управления проектами. .

  18. Каждый год в течение сентября проводится Тюменский инновационный форум «НЕФТЬГАЗТЭК».
    Форум посвящен определению механизмов инновационного роста отраслей топливно-энергетического комплекса, рассмотрению а также поиску заключений, образованию наилучших условий для формирования инноваторских проектов. Ежегодный тюменский форум представляетсобой важной дискуссионной площадкой по продвижению нефтегазовой ветви в Российской Федерации, имеет большой статус и своевременность, созвучен общей стратегии развития инноваторского направления в Российской Федерации
    https://neftgaztek.ru/

  19. Хотите лучший звук в вашем авто? Закажите сабвуфер на заказ
    Изготовление сабвуферов на заказ – sabvufer-audio.ru .

  20. Сколько уже денег и времени потратила, а толку ноль.
    Решила попробовать лазерную эпиляцию в клинике CleanSkin. Сильно не надеялась на результат. Но после нескольких сеансов.
    Исчезло вечное раздражение на коже. Не ожидала, что эффект будет таким хорошим.

  21. Секреты успешного полного протезирования для здоровой челюсти, поможет вам забыть о проблемах с челюстью и наслаждаться жизнью.
    Поменять все зубы цена https://polnoe-protezirovanie.ru .

አስተያየትዎን ያስቀምጡ

Your የኢሜል አድራሻ አይታተምም። Required fields are marked *