በእውነት ይህንን የሚመስል አዋጅ ሰምተን እናውቃለን? ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን የምሥራችን ያስከተለ ልደትን ማን ተወለደ? በመላው ዓለም ለሚገኙ የሰው ልጆች ሁሉ “ተወልዶላችኋል” ተብሎ ዜና ልደቱ የተነገረለትስ ማን አለ? ሔዋን በምድር ላይ መውለድን በጀመረች ጊዜ ይህ ዐዋጅ አልነበረም። ሣራም በእርጅናዋ ወራት ፀንሳ በወለደች ጊዜ “ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁ” የሚል መልአክ አልተላከልንም። ከሔዋን በፊት በምድር ላይ ፀንሳ የምትወልድ ሴት አልነበረችም። ከሣራም በፊት በእርጅናዋ ጊዜ የወለደች ሴት አልተገኘችም። ነገር ግን ይሄ ሁሉ ነገር ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን የምሥራችን ይዞልን አልመጣም። ምክንያቱም የተወለደው ክርስቶስ አይደለምና። ልደታቸው ለመደነቅ ምክንያት የነበረው ልደት ነው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የእናቱን ማኅፀን ከፍቶ የሚወጣ ልጅ ልደቱ ሊደነቅ ይገባዋል በምድር ላይ መኖር የጀመሩት አዳም እና ሔዋን በዚህ መንገድ አልተገኙምና። በምድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘጠኝ ወራትን ፀንሳ የወለደች ሴትንም ማየት ያስደንቃል አዳም ሔዋንን ከጎኑ ባስገኛት ጊዜ እንዲህ ያለ ሥርዐት አልነበረምና። በእርጅናዋ ወራት በመውለዷ የሣራም ፅንስና የይስሐቅ ልደት እንዲሁ አስደናቂ ልደት ነበረ። እናቱ ሣራ ስለ ይስሐቅ ስትናገር “እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህን የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል” ዘፍ 21፥6 ብላለች። ይሁንም እንጅ የወለደችው ልጅ ለሰሙት ሁሉ ሳቅ የሚሆንላቸው በእሷ ምክንያት ነው እንጅ በተወለደው ልጅ ምክንያት አልነበረም። በዘጠና ዓመቷ ወልዳለችና። ከወለደችም በኋላ “ደግሞም ሣራ ልጆችን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው? በእርጅናው ልጅን ወልጄለታለሁና” ብላ የምሥራቹን ወደ አብርሃም ልካለች እንጅ ለዓለም ሁሉ የምሥራች ተብሎ አልተነገረም።
ከዚህ ሁሉ የተሻለ የደስታ ዜናን የያዘው የመጥምቁ ዮሐንስ ልደት ነው “በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” ሉቃ 1፥14 ተብሎለታልና። ጊዜው የክርስቶስ ልደት እየተቃረበ የነበረበት ወቅት ነበርና በመወለዱ ተድላ ደስታን ለብዙዎቹ የሚሰጥ ፅንስ ከሴቶች ማኅፀን መገኘት ጀመረ። ነገር ግን ደስታው ከወገኖቿና ከጎረቤቶቿ ከዘመዶቿም ያለፈ አልነበረም “ጎረቤቶቿም ዘመዶቿም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው” ተብሏልና ሉቃ 1፥58። ሌሎችም አሉ መልካም እንደሆኑ አይተው ሰዎች የራሩላቸው፣ ባዕዳን የወደዷቸው ነበሩ ዘፀ 2፥2፣6 ነገር ግን ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምሥራች ይዘው አልመጡም። ስለዚህ ዐዋጅ ነጋሪ መልአክ መጥቶ “ደስ ይበላችሁ” አላለንም፤ ከእነሱ መካከል እኛን ሊያድን የተወለደ መሢሕ የለምና። እነዚህ ሁሉ የእናትና የአባቶቻቸውን ርስት ወርሰው ይኖራሉ እንጅ እኛን ሊያወርሱን የሚችሉት ርስት የላቸውም። በታላቅ ደስታ እንደሰት ዘንድ ምን ምክንያት አለን? እነዚህ ሁሉ ልጆችን ወልደው ምድርን ቢሞሏትም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጀምሮ የተገፋችውን መንግሥተ ሰማያት ለተገፉት ሐዋርያት ማውረስ የሚቻለው ማንም አልነበረም ማቴ 11፥12።
ዛሬ ግን ለሁሉም የሚሆን ልደትን የተወለደ የክርስቶስን ልደት እንሰማ ዘንድ እግዚአብሔር መላእክቱን ላከልን። ድንግል በድንግልና ፀንሳ እንደምትወልድ ትንቢት የተናገረ ኢሳይያስ ዛሬ በምድር ላይ የለም። እግዚአብሔር በተዘጋ በር ሳይከፍት ገብቶ ሳይከፍት ሲወጣ በራዕይ ያየው ባለ ራዕዩ ሰው ሕዝቅኤልም በአጠገባችን አይደለም። ጌታ የተወለደባትን ስፍራ “አንች ቤተ ልሔም የይሁዳ ነገሥታት ከነገሡባቸው አህጉር ብትበልጪ እንጂ አታንሺም” ብሎ ቦታውን ያሳየን ሚክያስም ቤተ ልሔም ላይ አልታየም። እነዚህ ሁሉ ትንቢት የተናገሩለት መሢሕ እስኪመጣ ድረስ በዚህ ዓለም ሆነው አልጠበቁትም በመቃብር ሞት እየገዛቸው የተነገራቸው ተስፋ ይጠባበቁ ነበር እንጅ አንዳቸውም በምድር ላይ አልነበሩም። ስለዚህም እግዚአብሔር መላእክትን ልኮ ዜና ልደቱን ነገረን።
በዳግመኛ ምጽአቱ ጊዜ በመላእክት አለቃ ድምጽ የሚቀሰቅሰን ነውና ዛሬም የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ልኮ ወደ ልደቱ ጠራን 1ተሰ 4፥16። ዛሬ ተወልዶ ያየነው በኋላ ከሰማይ ሲወርድ የምናየው ክርስቶስ ነው። አሁን “እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ” ብሎ የነገረን መልአክ በኋላም በነጋሪት ድምጽ ከመቃብራችን የሚቀሰቅሰን መላክ ነው። ዛሬ አዋጅ ነጋሪው መላክ የተላከው የተወለደውን ክርስቶስን ሊያሳየን ነው በኋላም የሚላከው ከሰማይ የሚወርደውን ክርስቶስን ወርደን እንድንቀበል ነው። አሁንም ክርስቶስ በኋላም ክርስቶስ። በኋላ በእልፍ አእላፍ መላእክት ታጅቦ በታላቅ ግርማ ተከቦ የሚመጣውን ክርስቶስን ዛሬ በግርግም ተጥሎ አየነው። ይህ ቀን ለእኛ ከቀናት ሁሉ የሚበልጠው ቀን ነው። ይህንን ቀን እስካሁን ካለፉት ቀናት በየትኛው ቀን ታመሳስሉታላችሁ? ዓለም በተፈጠረባት ቀን ነውን? ወይስ አዳምን በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው በተባለው ቀን ነው? ሕዝቡን ነጻ ያወጣቸው ታላቁ ሰው ሙሴ በተወለደበት ቀን ነውን ወይስ ነገሥታቱ ዳዊት ሰሎሞን በተወለዱበት ቀን ነው? በእውነት ለዚህች ቀን ምሳሌ ሊሆን የሚችል ቀን ከየት እናገኛለን?
ሰማይና ምድር የተፈጠሩበትን ቀን እንዳናደንቅ የሚያልፉበትም ቀን አላቸው ማቴ 24፥35 ቅዱሳን ወርሰውት የሚኖረውና የማያልፈው ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ተወልዶልናል። በሰማይና ምድር የልደት ቀን ያልነበርን እኛ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ልደት ሲከበር በክብር ተጠራን። ሔሮድስ ለልደቱ ዘፍነው ደስ የሚያሰኙትን እንጅ እኛን ሁላችንን አልጠራንም ክርስቶስ ሲወለድ ግን ሁሉም ተጠርቷል። ልደቱን የምናከብርለት ክርስቶስ እንደ ሔሮድስ ዘፍነን ደስ እንድናሰኘው የሚፈልገን አይምሰላችሁ በመወለዱ ለሁላችን የሚሆን ታላቅ ደስታን የምሥራችን ሊሰጠን ነው እንጅ። በዕለተ ልደታቸው በልተው ጠጥተው ከወገኖቻቸው ጋር ደስ የሚላቸው ብዙ ናቸው ዳን 5፥1 ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታን ስለሚሰጡ ልደታቸውን የምናከብርላቸው ልጆችን የወለዱልን ሴቶች ግን የሉም።
አዳም በተፈጠረበት ቀን በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯልና ደስ ብሎን ነበር፤ ነገር ግን ከዚያ የሚበልጥ ነገር ዛሬ ተደረገልን፤ እግዚአብሔር እራሱ በአዳም መልክ ተወለደልን። ይህንን ለማየት ወደ ቤተ ልሔም የማይሄድ ማነው? ኑ እስከ ቤተ ልሔም እንሂድ በኢሳይያስ የተጻፈችውን ድንግል እናገኛታለን። ኑ! ሁላችንም እንሂድ ድንግልናዋን ሳትለቅ እናት የሆነችውን ሴት አይተን እንደነቃለን። ኑ! እንሂድ፥ በሰማይ ያለ እናት የተወለደውን በምድር ያለ አባት ተወልዶ እናገኘዋለን። ሰማያዊ አባት ያለውን ክርስቶስን ከምድራዊት እናቱ ተወልዶ እናየው ዘንድ ኑ! እሳት በጨርቅ ሲጠቀለል አይተን እንድናደንቅ ኑ! የልዑል ኃይል የፀለላት፣ መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ሴት ዛሬ በመካከላችን ናት ኑ እናክብራት። ማን ያሳየናል ብለን እንዳንቀር የሰማይ ከዋክብት ሳይቀሩ ወደዚህ ስፍራ እየመሩ ይወስዳሉ።
እመቤታችን ጌታን በወለደችበት ቀን በእንግዶች ማረፊያ መብል መጠጥ ቀርቦ ዘፈን ጨዋታ ይደረግ ነበር። ዛሬ መብል መጠጥ ተሰናድቶ ዘፈን ጨዋታ የሚደረግባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ቅዱስ ሉቃስ “በእንግዶች ማረፊያ ለማደሪያ ስፍራ አልነበራቸውምና” ሉቃ 2፥7 ብሎ የገለጻቸው ስፍራዎች ናቸው። ለእኛ በእንግዶች ማደሪያ ካሉ ሰዎች ጋራ መዝናናት ምን ያደርግልናል? የዓለም በኵር ክርስቶስ የተወለደው እኮ በእንግዶች ማረፊያ ውስጥ አይደለም። ጌታ የተወለደው ለእኔ ነው የሚል ሁሉ በዓሉን ጌታ በተወለደበት ግርግም ተገኝቶ በዝማሬ ማክበር ይገባዋል። እስኪ ተመልከቱ በዚያ ቀን በዓሉን ካከበሩት መካከል ክርስቶስ ወዳለበት ቦታ ያልሔደ ማነው? መላእክት፣ ነገሥታት፣ ኖሎት፣ እንስሳት ሁሉ ተገኝተዋል። እኛ ግን ልደቱን ለማክበር ጌታ ወዳልተወለደበት ስፍራ ለምን እንሔዳለን? ምንም እንኳን ለማኅሌት የሚሆን መዝሙር ባናጠና እስትንፋስ ካለን በቂ ነው። እስትንፋሳቸውን ያሟሟቁት እንስሳት ሳይቀር በቅዱስ ወንጌል መጻፋቸውን አትርሱ። ወርቅ በሳጥናቸው ካመጡለት ነገሥታት እኩል ባዶ እጃቸውን የመጡ እረኞችን ታሪክ ስናገኘው አይገርማችሁም? እግዚአብሔር የሚፈልገው በተወለደበት ቦታ ልደቱን እንድናከብር ነው እንጅ ሌላ አይደለም። አዕላፍ መላእክት በሚዘምሩበት ቀን የአዕላፋት ዝማሬ ከተማችንን ሊሞላት ይገባል። ዕልፍ አዕላፋት ሆነን ከዕልፍ አዕላፋት መላእክት ጋር የምናገለግልበት ቀን ደረሰ። ኑ የመላእክትን እንጀራ ተመገቡ፤
ማስታወሻ:- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆኑ የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው:: ሊቅ ሊቃውንት የጃንደረባው ሚዲያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ሰኞ የሚነበቡ ይሆናል::
ቃለ ህይወት ያሰማልን
ቃለ ህይወት ያሰማልን።
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ጸጋቸውን ያብዛልን
ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
ቃለ ህይወትን ያሰማልን።
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ የደረሷቸው መፃህፍት ካሉ የሚነግረኝ ይኖራል?
ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ🙏
Купить двери на заказ в Москве
Производство дверей на заказ по индивидуальным размерам
Советы по выбору дверей на заказ
Материалы и цвета дверей на заказ
Двери на заказ: доставка и монтаж дверей на заказ
Бюджетные варианты дверей на заказ
Ламинированные двери на заказ: преимущества и недостатки
Металлические двери на заказ: надежность и безопасность
Двери на заказ для спальни
выбор дверей [url=http://mebel-finest.ru/]http://mebel-finest.ru/[/url].
እኔ የኢትዮጵያ ጀንደረባ አባል ነኝ
ቃለ ሕይዎት-ያሰማልን!!!
እኔ ውጭ ነኝ ግን የዚህ ሚዲያ አባል መሆን እፈልጋለሁ