ኢጃት ጠቅላላ ማኅበር ሆነ

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) ማኅበር በጠቅላላ ማኅበርነት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምስክር ወረቀት ተቀበለ:: ታኅሣሥ 11 2013 በፊልጶስ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መጽሐፍ ምርቃትን በማካሔድና የመጻሕፍት ጉባኤን በማካሔድ የተመሠረተው የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በተመሠረተበት ቀን ልክ በሦስተኛ ዓመቱ ታኅሣሥ 11 2016 ዓ.ም. የጠቅላላ ማኅበርነት የምስክር ወረቀትን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የማኅበራት ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ሊቀ ጳጳስ እጅ ተቀበለ::

አስቀድሞ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ሙሉ እውቅና አግኝቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ማኅበሩ መምሪያው ለነባርና አዳዲስ ማኅበራት ያቀረበውን “ሕጉን ተከትላችሁ አገልግሉ” የሚል ጥሪ ተቀብሎ በቤተ ክርስቲያኗ ዶግማ ፣ ቀኖና፣ ትውፊት፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ደንቦችና መመሪያዎች በመመራት መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት በማኅበራት አስተዳደር ደንብ ቁጥር ፫/፳፻፲፭ አንቀጽ ፲፯ መሰረት ማኅበራት ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት እና ዝግጅት ሲያሟላ ቆይቶአል:: በመሆኑም ዛሬ ታኅሣሥ ፲፩/፳፻፲፮ ዓ.ም ዋናው ማዕከል በመገኘት ከመምሪያው ሊቀዻዻስ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአገልግሎት ፈቃድ የምስክር ወረቀቱን ተቀብሏል፡፡

የምስክር ወረቀቱን የተቀበሉት የኢጃት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ እንደገለጹት ልክ የዛሬ ፫ ዓመት ታኅሣሥ ፲፩ ቀን በቅዱስ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን በተካሄደ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መጽሐፍ ምርቃት ጉባኤ የተወጠነው የኢጃት የአገልግሎት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሐምሌ ፲፩/፳፻፲፫ ዓ.ም ጊዚያዊ ዕውቅና ቀጥሎም ሰኔ ፲፯/፳፻፲፬ ዓ.ም ሙሉ ዕውቅና አግኝቶ በ፳፪ ቤተሰባዊ መዋቅሮች አገልገሎቱን ሲያከናውን እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡

አያይዘውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ለመደገፍ የቅዱስ ባኮስን መንገድ የተከተለ እና እነሆ ውኃ ብሎ ከችግር ይልቅ መፍትሄን በማመላከት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ከዛሬ ሶስት ዓመት ጀምሮ እየተንቀሳቀሰ ለቆየው ኢጃት በዛሬው ዕለት የተሰጠው የአገልግሎት ፈቃድ ለበለጠ የአገልግሎት ጉልበት የሚሰጥና አደራ የሚጥል ነው፡፡ ጠቅላላ ማኅበር ሆነን መመዝገባችንም በጥቂት ሀገረ ስብከቶች ብቻ የተወሰነውን አገልግሎት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ትልቅ ዕድል ነው:: የምንችለውን ያህል ቤተ ክርስቲያናችን የጣለችብንን አመኔታ ለማክበርና አደራችንን ለመወጣት እንጥራለን በማለት ደምድመዋል::

Share your love

8 አስተያየቶች

  1. Egziabher yetemesgen yhun. Yhennm lelochunm bego alama yalachewn mahberat egziabher ytebkln yabzaln srachunm ybarklachu. Be 5th generation lay tesatfe aychalew ena Ewnet lemenager ye 3 amet sra bcha aymeslm egziabher dkamachun kotro egnan freama yarglachu.
    Egziabher yakbrlgn!

  2. በጣም ደስ ይላል እንኳን ደስ አለን በተለያዩ መርሀግብሮቻችሁ ላይ መሳተፍ እፈልጋለሁ እግዚአብሔር ይርዳኝ

  3. ” የምንችለውን ያህል ቤተ ክርስቲያናችን የጣለችብንን አመኔታ ለማክበርና አደራችንን ለመወጣት እንጥራለን ”

    እግዚአብሔር ይርዳን

  4. እንኳን ደስ አላችሁ ከዚህ የበለጠ ተግታችሁ በአገልግሎት እንድትበረቱ አምላከ ቅዱሳን ብርታቱን ያድላችሁ

አስተያየትዎን ያስቀምጡ

Your የኢሜል አድራሻ አይታተምም። Required fields are marked *