ሱባዔ ጉባኤ መጋቢት 15 ሊጀመር ነው::

አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) ከዚህ ቀድሞ ለአምስት ዙር ሲሠጠው የነበረው የሱባዔ ጉባኤ ትምህርት በዚህ ዓቢይ ጾም በሦስት አድባራት ሊካሔድ እንደሆነ ተገለጸ:: 

በየአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እና የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጠቅላላ ማኅበር  (ኢጃት) በ2015 መጨረሻ ላይ በጋራ ሊሠሯቸው ከተፈራረሙባቸው ሦስት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ሱባዔ ጉባኤን በትብብር ለማካሔድ ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቅቆአል:: 

በሕገ ቤተ ክርስቲያን በመዋቅር ወጣቶችን ማስተማር  ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተሠጠ ኃላፊነት እንደመሆኑ ሱባኤ ጉባኤን ከሥርዓተ ትምህርቱ ጀምሮ ከትምህርቱ በኋላ ስለ ተማሪዎቹ ሁኔታ ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርት ጋር የሚኖራቸውን ቀጣይ ቆይታና የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የባላደራነት ሚና በዝርዝር ለአንድ ዓመት ያህል በአግባቡ ሲያጠና እንደነበር ተገልጾአል::  በሒደትም ተተኪ መምህራንን በጋራ በማብዛት ሙሉ በሙሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የሚረከብበትን ዕቅድም አዘጋጅቶአል:: 

በዚህም መሠረት ከፊታችን መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የሚካሔደው ይህ የትምህርት ሱባኤ 

በሚከተሉት ሦስት ሥፍራዎች ይካሔዳል::

፩) ከመጋቢት 15 /2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 15/ 2016 ዓ.ም በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት

፪)  ከመጋቢት 17 /2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 17/ 2016 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት

፫) ከመጋቢት 19 /2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 19/ 2016 ዓ.ም ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት

በዚህም መሠረት የተመሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው online ላይ በሚሞላ የምዝገባ ቅጽ ነው። ሙሉውን የምዝገባ ቅጽ (link) የፊታችን ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ በጃንደረባው ሚዲያ የቴሌግራም ገጽ ይለቀቃል።

ትምህርቱ ጨርሶ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ትምህርት ተምረው ለማያውቁ  የተዘጋጀ መሆኑን አደራ እያልን ያለው ቦታ ውስን በመሆኑ ተሽቀዳድማችሁ እንድትመዘገቡና ካመለጣችሁ ደግሞ ሌላ ዙር በትዕግሥት እንድትጠብቁ የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እና የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ አደራ ይላሉ::

በሦስት ቦታዎች የሚደረገው የመጀመሪያውን ዙር የጋራ ሱባዔ ጉባኤ እንደ ሙከራ ፕሮጀክት (pilot program) የሚካሔድ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም አጥቢያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድና ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሁሉ የሚረከቡት ወጣቶችን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመማረክ የተዘጋጀ የወንጌል መረብ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው

#ወደ_ሠረገላው_ቅረብ

Share your love

39 አስተያየቶች

  1. እግዚአብሔር ይስጥልን!

    “ትምህርቱ ጨርሶ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ትምህርት ተምረው ለማያውቁ  የተዘጋጀ መሆኑን” የሚለው ትንሽ ቢብራራልን? በሰንበት ትምህርት ቤት ወይም በጊቢ ጉባኤ ተሳትፈን የማናውቅ መሆን አለብን?

  2. በእውነቱ ዘመኑን የዋጀ ነው ብንዘገይም አሁንም አልመሸም እና የግል አስተያዬቴ መርካቶ ያለው ደብረ አሜን ተ/ ሐይማኖት አብዛኛው ወጣት እዛ አካባቢ በብዛት ስላለ የትራንስፖርት ጉዳይም ከግምት በማስገባት ቢታይ እላለው በተረፈ ፀጋውን ያብዛልን።
    ወልደ ሠንበት ነኝ
    ከአሽዋ ሜዳ ደብረ ምህረት ቅ/ ላሊበላ ቤ/ ክርስቲያን

    • በጣም ደስ ይላል
      ነገር ግን በዚ ጭንቅ ሰዓት ኦርቶዶክስ ጠል የሆነ: የኢትዮጵያን ባህል: ወግና ትውፊት አውዳሚ የሆነ መንግስት አስቀምጠን እኛ ተምረን እምንጠፋ ከሆነ ለምን እንማራለን? መጀመሪያ ለኦርቶዶክስ እምትመች መንግስት መመስረት አለበት ብዬ አምናለሁ:: ይህ የሚሆነው ደሞ በትምህርት አደለም:: ፖለቲካ በመሳተፍ እንጂ በመኳኳል ወይም ሰው እየተጨፈጨፈ ነጭ ለብሶ በመዘመር አደለም:: ቢታሰብብት ጥሩ ይመስለኛል በርግጥ ታስቦበት ይመስለኛል በዚ ሰዓት ብቅ ያላችሁት:: አሁን አትረብሹን ስራ ላይ ነን::

      • ችግሩ እኮ ይሄ ነው የክርስትና ዓላማ ያልገባው ሰው የቤተክርስቲያንን ዓላማ ከፖለቲካ ጋር አቀላቅሎ ነው የሚረዳው ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ እንሁን መማር አለብን ማስተማር አለብን ዝማሬውም ይቀጥላል እግዚአብሔር የአንዳንድ ጊዜ አምላክ አይደለም የሁልጊዜ እንጂ ገና አዲስ መንግስት እስክንመሰርት ብለን ሁላችንም ፓለቲከኛ መሆን የለብንም ቤተክርስቲያን የሰማይ መንግስት በምድር ላይ ናት እኛ ንጉሳችን እግዚአብሔር ነው ስለዚህ የትምህርትን ጥቅም ብትረዱ ጥሩ ነው እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጠን

        • በጉጉት ነው የምጠብቀው እግዚአብሔር ይርዳኝ ለመማር🙏🙏🙏🙏

  3. በጣም ደስ ብሎኛል ይሄንን በመስማቴ ነገር ግን ከስራ ጋር መማር ላሰብን ሰዎችስ እንዴት ነው የሚሆነው?

  4. በእዉነቱ በጣም በጉጉት ስጠብቀዉ ነበር እግዚአብሔር ያበርታችሁ። በዕለቱ ብዙ ተመዝጋቢዎች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ ሞላ እንዳንባል እፈራለሁ።
    ኃይለ ሚካኤል ነኝ
    ከደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን።

  5. በእዉነቱ በጣም በጉጉት ስጠብቀዉ ነበር እግዚአብሔር ያበርታችሁ። በዕለቱ ብዙ ተመዝጋቢዎች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ ሞላ እንዳንባል እፈራለሁ።
    የብዙዎቻቹ ጥያቄ ሰዓት ነው እና 5ኛ ዙር የተማሩ እንደነገሩኝ ከ12:00 – 2:00ሰዓት ነው።
    ኃይለ ሚካኤል ነኝ
    ከደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን።

  6. Ejat is an incredible…. What about Christians who live abroad they are asking for online platforms they want to be part of the Ethiopian jandrebaw team and also want to learn “Subaie the gubaie”. Thankyou

  7. ደስ ይላል ። በሁሉም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያኖች ቢጀመር ጥሩ ነበር ። እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን ።
    አሜን

  8. በሁለም አጥቢያዎች መታሰቡ መልካም ነው።
    መድሐንያለም ያሳካልን

  9. በጉጉት ስጠብቀው ነበር እግዚአብሔር ይርዳን ! የአምላክ ቸርነት የእመብርሃን ምልጃ የቅዱሳን ተራዳዒነት ከእናንተ ጋር ይሁን ፡፡

  10. የትራንስፖርት ችግር አለ እባካቹ ከተቻለ አንድ ቦታ ቢሆን
    የአእላፋት ዝማሬ ላይ ያገጠመን ችግር ይህ ነው ቤት ለመድረስ ከ 1 ሰዓት በላይ የሚፈጅብን ሰዎች አለን 🙏🙏
    እግዚአብሔር ይስጥልኝ!

  11. መጀመሪያ እግዚአብሄር ይስጥልን፤ አስተያዬቴ መርካቶ ያለው ደብረ አሜን ተ/ ሐይማኖት አብዛኛው ወጣት እዛ አካባቢ በብዛት ስላለ እዛም ቢስጥ እላለው እባካችሁ አስቡበት አመሰግናለው

  12. እየሰራችሁ ባላችሁት ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ

  13. በጣም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ ፕሮግራም ነው ደስ ብሎናል እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ያስፋው ተባረኩ!!!
    መርካቶ እናአካባቢው ላለን ሰዎች ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል : ደ/ኃይል ቅ/ራጉኤል ፡ ደ/አሚን አቡነ ተ/ኃይማኖት ወይም ደ/መዊዕ ቅ/ሚካኤል ቢዘጋጅልን ለትራንስፖርትም …… እንዲሁም ሰዐቱ ቢገለፅ መልካም፡፡

  14. እግዚያብሔር በጎ ሃሳባቹን ወዶና ፈቅዶ ይቀበላቹ። እኛንም ለመማር ያድለን

  15. እግዚአብሔር ያክብርልኝ በጣም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ መርሐግብር ነው፤ ትምህርቱ የሚሰጥበት ጊዜ በትክክል ቢገለጽ መልካም ነው

  16. ፈጣሪ ለኔ የላካቹ ነው የ ሚመስለኝ በጣም ደስ ብሎኛል ለ መማር በጉጉት እየጠበኩ ነው፡፡

  17. ዘመኑን የዋጀ ስራ ነው ። እኔ እምጠይቀው በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ለመገኘት እንዲያስችል ሰዐቱ ቢገለጽ።እና ደግሞ እድሜ ገደብ ካለው ብታሳውቁ።
    እግዚአብሔር ሀሳባችሁን ይሙላላችሁ እኛንም ለቤተክርስያን የምንተርፍ ያድርገን።

  18. በጣም የተባረከ ሃሳብ ነው። ሁላችንንም የሚቀይር ቆይታ ያድርግልን። እግዚአብሔር ይጠብቀን።

  19. በመጀመሪያ ጃንደረባው እያደረ ያለው ነገር በጠቅላላ የሚደገፍ እና የሚያስመሰግን ነው። አብዛኛዉ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እኔን ጨምሮ ማለት ይቻላል ለሀይማኖቱ ጥልቅ ፍቅር ያለው ቢሆንም እውቀቱ ግን በቂ አይደለም ብዬ አስባለሁ ለዚህም ከሌሎች ሀይማኖት የሚሰነዘረውን ጥያቄ መመለስ የምንቸገረው ስለዚህ ሁላችንም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ለዚህ የተባረከ ሚዲያ በሁሉም መንገድ በመደገፍ ሀይማኖታችን መጠበቅ ለትውልድእውነተኛውን እውቀት እንዲተላለፍ ማድረግ ይኖርብናል እላለሁ። ከምስጋና ጋር ወስናቸው

  20. [url=https://ritualsm.ru/lgoty.html]Правила получения государственного пособия на погребение Москва[/url] или [url=https://ritualsm.ru/grob.html]Гробы для похорон престиж класса[/url]

    [url=https://ritualsm.ru/anosinskoe-kladbise.html]Пакеты услуг Аносинское кладбище[/url]

    https://ritualsm.ru/groby-dla-zivotnyh.html

    Ещё можно узнать: [url=https://ritualsm.ru/venki.html]Венки на похороны с хризантемами[/url]

    Катафальный транспорт Анкудиновское кладбище

  21. ቢዘገይም አሁንም ቢሆን ጥሩ ሰዓት ላይ ደርሳችሁልናልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እንድንማር ጌታ ይፍቀድልን አሜን።
    የኔ ጥያቄ ግን ምንም አይነት ትምህርት ከዚህ ቀደም ያልተማረ የተባለው ሀሳብ ላይ ነው ችግሩ ቢገለፅልን ?
    እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  22. ከሀገር ውጭ ያለነውን ተሳታፊ የሚያደርገው የሱባኤጉባኤ ፕሮግራም እና እቅድ እምን ደረሰ በጉጉት እየጠበቅን ነው እባካቹ አትርሱን

አስተያየትዎን ያስቀምጡ

Your የኢሜል አድራሻ አይታተምም። Required fields are marked *