ሕይወት ነክ መጻሕፍት መብዛት አለባቸው

የአርባ አራት መጻሕፍት መተርጉም ፣ ጸሐፊና ሰባኪ ከሆነው ከመምህር አያሌው ዘኢየሱስ ጋር በጃንደረባው ሠረገላ ላይ ወግ ጀምረን እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሁለተኛው ክፍል እንዲህ ይነበባል፡፡

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- ሁሉም የአቡነ ሺኖዳ አይደሉም፡፡ ምናልባት ሃያ ያህሉ የእርሳቸው ይሆናሉ፡፡የሌሎች አባቶችም አሉ ። የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሁለት መጻሕፍት አሉ ፣ ሀብታምና ደሃ የእሱ ነው።  ሌላም ‘ወጣቶችና የንጽሕና ሕይወት’ አሁን በግብፅ ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ጳጳስ የሚባሉት የእሳቸው ነው። ‘የክርስቲያን ቤተሰብ’ም እንዲሁ፡፡ የሚበዙት ግን የአቡነ ሺኖዳ ናቸው።  አሁን ለምሳሌ የበረሀ አባቶች ምክሮች እንግሊዘኛውን የተረጎመችው ሲስተር ብኔክታ ዋርድ ናት፡፡ የግብፃዊት እናት ናት ፤ አረብኛውን ወደ እንግሊዝኛ እሷ ናት፡፡ እኔ ደግሞ እሱን ነው የተረጎምኩት፡፡

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- መጀመሪያ መጽሐፉን ደጋግሜ አነበዋለው፡፡ ቢተረጎም ለምዕመናን ቢደርስ ይወዱታል ወይ? ይህ መጽሐፍ እኔን ሰብኮኛል ወይ? ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ የእሳቸውንም ሆነ የሌሎች አባቶች መጻሕፍት ለመተርጎም ዋናው መሥፈርቴ ይህ ነው።  ይህ መጽሐፍ ለእኛ ሕዝብ ያስፈልገዋል ፣ የሕይወት መጽሐፍ ነው እና መተርጎም አለበት ብዬ ከወሰንሁ እጀምረዋለው ። መተርጎም ከመጀመሬ በፊት በሰላም አስጀምረህ በሰላም አስጨርሰኝ ብዬ ጸሎት አደርሳለው። አንዴ ቁጭ ካልኩኝ ካልጨረስኩት አልነሣም፡፡ የፈለገ ነገር ቢመጣ ሌላ የተሻለ የሚባል መጽሐፍ እንኳን ቢመጣ ይቀመጥ ነው የምለው፡፡ ሰሎሞን ‘ለሁሉም ጊዜ አለው’ ብሎ የለ? በአንድ ጊዜ አንድ ነገር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ‘ስትበላ ብላ ፣ ስትጫወት ተጫወት’ አንዱን መጽሐፍ ከያዝሁ ካልጨረስኩት አላቆምም፡፡ እግዚአብሔር ይረዳኛል እጨርሰዋለሁ። በቶሎ ነው የሚያልቀው፡፡ አነስ አነስ ያሉት መጽሐፎች አንድ ወርም አይፈጁብኝም፡፡ በስድስት ሰባት ቀን እጨርሳለሁ፡፡ ተለቅ ዳጎስ ያሉትን መጻሕፍት ለመተርጎም ደግሞ አንድ ወር ተኩል ይፈጅብኛል።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- አዎ ፤ አሁን አንድ ጊዜ ጊዜውን በውል አላስታውሰውም 2006 ላይ ይመስለኛል። በአንድ ዓመት ውስጥ አራት መጻሕፍት ተርጉሜያለሁ፡፡ አነስ አነስ ያሉ መጻሕፍት ናቸው። አንዳንዱ ደግሞ ተለቅ ያለ ሆኖ የማይገፋ መጽሐፍም ሊኖር ይችላል ። አንድ መጽሐፍ ቢበዛ ከሁለት ወር ግን በጭራሽ አያልፍም።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- አግኝቼያቸዋለሁ፡፡ ይሄንን ብዙ ሰዎች አያውቁም፡፡ ፋና ብሮድካስት ለፋሲካ ባዘጋጀው የሬዲዮ ፕሮግራም ጋዜጠኛ አዳም ታደሰ ጋብዞኝ እዚያ ላይ ብቻ ተናግሬያለው። በአባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ ብርታት በ2000 ዓ.ም. ላይ የኛ ሚሌኒየም ሲለወጥ ማለት ነው የዚያን ጊዜ መጥተው ነበረ። እኔ ተከራይቼ የምንኖረው ዓለም ባንክ ሚባል ሰፈር ነበር፡፡ ደብረ ብሥራት ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ የሆነ ዮሴፍ አረጋ የሚባል ልጅ እንደሚመጡ ነገረኝ ። በተባለው ሰዓት መጡ ቤተ ክህነት ፕሮግራም ነበራቸው። ለብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ደውዬ ላገኛቸው እንደምፈልግ ነገርኳቸው ። ፕሮግራማቸው የተጣበበ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን እና ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ያናግራሉ፡፡ ጊዜ ካገኘሁ እነግርሃለው አሉኝ። ከእሳቸው ጋራ ቀጠሮ ይዤ ቁጭ አልኩ።

       በማግሥቱ ቅዳሜ ቀን ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ለአቡነ ቴዎፍሎስ ሐውልት አበባ አስቀመጡ፡፡ ከዚያ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ጸሎት አድርሰው ችግኝ ተከሉ፡፡ እዚያው ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ እና በመጡበት ፍጥነት ሄዱ፡፡ ታጅበው ነበር። ፕሮቶኮል ሹሙ አያስጠጋም። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያየዋቸው። ዕንባዬ ነበር የመጣው፡፡ የዚን ጊዜ ገና ሰባት ስምንት መጽሐፍ ነበር የተረጎምኩላቸው። በሚቀጥለው ቀን ቦሌ መድኃኔዓለም ፕሮግራም አላቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እና በፕሬዝዳንቱ ጋር  ከዚያ በኋላ የፎቶ ፕሮግራም ነበራቸው። ብፁዕ አባታችን ‘በዚህ ትንሽ ደቂቃ ኮንትራት ታክሲም ቢሆን ይዘህ ና’ አሉኝ። በጓደኛዬ መኪና ሁለት ሌሎች ሰዎችን ጨምረን በብርሀን ፍጥነት ደረስን። ስንደርስ የማኅበረ ቅዱሳን ልጆች መዝሙር እያቀረቡ ነው። ገባን፡፡ አባታችን ተነሥተው  ሲዞሩ አዩኝ። ጥበቃው አላስገባ ሲለኝ ‘ልቀቁት እኔ ጋር ነው የመጣው’ አሉ ። ከአባታችን ጋር ስንሄድ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሁለቱም ወጥተው እኔን ለማግኘት ቆመው እየጠበቁኝ ነበር። ለኔ ለኃጢአተኛው ማለት ነው። እኔ ማን ነኝ? አሁን ሁለቱ አባቶች ሲጠብቁኝ ምን ይባላል? ብዬ እየፈራሁ ሔድኩኝ። አቡነ ሺኖዳ አጭር ናቸው፣ ቀጭን ናቸው፣ አይኖቻቸው ግን በጣም ብሩህ ናቸው፡፡ ከዚያ አወሩኝ። የተረጎምኩላቸውን መጻሕፍት ሠጠኋቸው። ‘እነዚህ በሙሉ ሕይወት ነክ መጽሐፎቼ ናቸው’ ። ዶግማቲክ የሆኑትን መጽሐፎቼንም ተርጉም’ አሉኝ። ጎንበስ በል ብለው አጥብቀው ይዘው ጸሎት አድርሰውልኝ ሄዱ።

       ትንሽ ነው ያወራነው ብዙ አላወራንም። እኔ ግን ልቤ ከእርሳቸው ጋር አብሮ ሄደ። አባቴ አቡነ መልከ ጼድቅ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም ጋር  እንድሳለም አቀረቡኝ። ተሳለምኩኝ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንድ መንፈሳዊ ልማድ አላቸው። ኪሳቸው ገብተው መስቀል አወጡና ሠጡኝ። ‘ሚስት አለችህ?’ አሉኝ፡፡ ‘አዎ’ አልኳቸው፡፡ ‘ይህ ደግሞ ለእሷ ይሁን’ ብለው እንደገና አውጥተው ሠጡኝ። ሕመሜን አስተውለው ‘የምትድን ልጅ ነህ ፤ ትድናለህ በርታ እና ሥራ ጎብዝ’  አሉኝ።

       ከዚያ ስወጣ በርሬ ብሔድ ደስ ይለኝ ነበር። ጓደኞቼን ማውራት ሁሉ አቃተኝ፡፡  ለረጅም ጊዜ ዝም አልኩኝ፡፡ የማይረሳ ቀን ነበር። እርሳቸውን ሁኔታቸውን በደንብ ያየሁበትን ሁኔታ ‘አቡነ ሺኖዳን በአካል አገኘኋቸው’ ብዬ አንድ ስድስት ሰባት ገጽ ጻፍኩኝ።

       ስለ እርሳቸው የሰማሁት ሌላ ነገር ግብፅ እስክንድርያ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ያለበት በየሳምንቱ ይሰብካሉ፡፡ ብዙ ሰው ነው የሚመጣው ፤ አስር ሺህ ድረስ ይመጣል ይባላል። አንዳንዴ ጥያቄ ይቀበላሉ በወረቀት ከኋላ ወደ ፊት እየተላለፈ ለእያንዳንዱ መልስ ይሰጣሉ።  አንድ ሰው ከዚያ ሁሉ ሕዝብ መካከል ‘በቀደሙት አባቶቻችን ዘንድ ተአምራት ይሠራ ይፈጸም ነበረ ፤ ብዙዎች ድነዋል፡፡ አሁን ግን ይህ ነገር አይታይም ፤ ተአምር የለም ፤ ለምንድን ነው?  ለዚህ ምን መልስ አለዎት?’ ብሎ በወረቀት ላከ። ተጠራጣሪ ሊሆን ይችላል፣ የሚፈታተን ሰው ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ኦርቶዶክስም ሆኖ ለመፈተንም ይሁን አይታወቅም።

       አቡነ ሺኖዳ ወረቀቱን አንሥተው አነበቡና ተነሥተው አቋርጠው በሕዝቡ መካከል ሄደው የጠየቀው ሰው ጋር ደርሰው አጠገቡ ቆሙ፡፡ ‘ተአምር ማለት ይሄ አይደለም?’ አሉት። መልስ ሠጡት ማለት ነው። ‘እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ሁሉ ተአምር ይፈጸማል ይደረጋል’ ብለውት ተመልሰው ሄዱ፡፡ ይህንን ስለ እርሳቸው ሰምቻለሁ፡፡

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- ይሄንን መልስ ለመመለስ መመዘኛ ሆኖ ማስበው እኔ የኅትመቱን ሁኔታ በመገመት ነው። በውጪ ሀገር አንድ መጽሐፍ አርባ ሚልየን ቅጂ ይታተማል፡፡ እንደገና ደግሞ በጣልያንኛ በፈረንሳይኛ ሲተረጎም ደግሞ የዚያን ያህል ነው። አንድ ሰው በጣም ብዙ መጻሕፍትን ያሳትማል።  የኛ ሲታይ ከሦስት ሺህ ወደ አምስት ሺህ የገባው ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው። እኔ አሁን  ‘የዲያቢሎስ ውጊያዎች ፣ የተራራው ስብከት’ ከወጣ በኋላ እየታወቅሁ ስሔድ የሚያነብ ሰው ሲጨምር ነው አምስት ሺህ ቅጂ የገባው። ‘የዲያብሎስ ውጊያዎች’ በጣም ስለተወደደ ዐሥር ሺህ ድረስ ታትሟል። የኢትዮጵያ ህዝብ ስንት ነው? ከመቶ ሚልዮን በላይ ነው አይደል? ምን ያህል ኦርቶዶክስ አለ? ሲባል አርባ ሚልየን ሊሆን ይችላል ። ሽማግሌዎችን ሕፃናትን ቀንሰን ደማምረን ብናስብ የሚያነበው ሰው በጣም ትንሽ ነው። የሚያነቡት ያነባሉ ፤ የሚያነቡት ሰዎች ቁጥር ግን አነስተኛ ነው። በዓመት አንድ ጊዜ ነው አንድ መጽሐፍ የሚታተመው፡፡ እርሱም ከፍተኛ አምስት ሺህ ኮፒ መጻሐፍት ነው።

       ሶሻል ሚድያ ሲመጣ ደግሞ የበለጠ አወረደው። አሁን ሰው መጽሐፍ ገልጦ ማንበብ ጊዜ ይገድላል ብሎ ያስባል። ሌላው በትረካም ደግሞ መቷል። ይሄ እንደ ዩ ቱዩብ የመሳሰሉት እዚያ ላይ ተደርጎላቸው ሲተኙ ነው የሚሰሙት። ብዙ ጊዜ ነጮች ለእኛ አንድ ነገር ሲሠሩ ሌላ አሉታዊ ነገሮችን ተፃራሪ ነገር አብረው ነው የሚሠሩት። እነርሱ የሚጠቀሙበትን ሌላውን የሚጎዳበትን ይሠራሉ፡፡ ጌምና ሌላ ሌላ አላስፈላጊ ነገር አብረው ይልካሉ። ሐበሻ ከሱ ጋራ ሲታገል ፈረንጅ ግን ያነባል፡፡ ባቡር ላይ መጸዳጃ ቤት ፣ ሥራ ቦታ፣  በመዝናኛ ቦታ መጽሐፍ ገልጦ ሲያነብ ነው የሚታየው፡፡ 

       የመጻሕፍት አለመሸጥ እና የማሳተሚያ ዋጋ መወደድ እኔንም ወደ ትረካው ዓለም አስገብቶኛል። በዓመት አራት ጊዜ የተለያዩ መጻሕፍት የማሳተም አቅሙ እያለኝ አሁን ግን በማሳተሚያ ዋጋ መወደድ ምክንያት አንድ ጊዜ እንኳን ማሳተም አልቻልኩም። ከዚህ እኔ የምረዳው ወይ የሚያነብ ሰው የለም ወይም ደግሞ ብሩ ጠፍቷል ኑሮ ተወድዷል። ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ ያም ሆነ ይህ ግን አንባቢ የለም ብዬ ነው ማስበው። የሚያረካ አይመስልም ፤ ከሌላ ሀገር ሲወዳደር ወርዷል። ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ማለቴ ግን አይደለም እግዚአብሔርም እንዳይታዘበን።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- ዶ/ር አለማየው ዋሴ እሸቴ እጅ ይባርክ የሚያስብል ሰው ስድስት መጻሕፍትን  ደርሷል። ‘ችቦ’ ይመስለኛል የመጨረሻው ፤ የእርሱን መጻሕፍት አነባለሁ እንደዚህ ዓይነት መንፈሳዊነትን ይዞ ማንኛውንም ነገር አካትቶ የሚገርም ጽሑፍ ነው የሚጽፈው። አንድ ሰው አንድ ነገር ሲጽፍ እኔ እንዲህ ሆኜ ፣ እዚህ ሔጄ ፣ እንደዚህ አድርጌ ብሎ ከትምህርቱ ፣ ከእውቀቱ ፣ ከፊልድ ሥራው ከልምዱ አድርጎ ሲጽፍ በገጠሙት ነገሮች ውስጥ እግዚአብሔርን ይሰብክበታል። ቤተ ክርስቲያንን ያሳይበታል። ምእመናንን ይሰብካል ። ሰዉ ደረቅ እውነት አይዋጥለትም ብዬ አስባለሁ።

       አሁን የአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ የሚወደዱት የሕይወት መጻሕፍት ስለሆኑ ነው። ዶግማቲክ የሆኑ ነገሮች አንድ ተርጉም ብለውኝ ነበር። አልተረጎምኩም እኔ አይቼዋለው ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ ስለ አምስት አዕማደ ምሥጢር ፣ ስለ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ስለ ሕግ እንደዚህ አይነት ትምህርቶች ሰዉ ተምሮ ነው ያደገው። አሁን ሰዉ የጎደለበት ሕይወቱ ነው። የሕይወት መጽሐፍቶች ስለሆኑ ነው እና ማንም እንደዚህ አይነት ነገር ቢፅፍ እንደ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ ፣ እንደ አቡነ ሺኖዳ ዓይነት መጻሕፍት ቢጽፍ ያዋጣዋል። ከገንዘብ አንጻር ሳይሆን ለሕይወት። ሕይወቱ ነዉ የጠፋው፡፡ ሰዉ የሚደባደበው ፣ የሚሰዳደበው ክርስቲያናዊ ሕይወት ስለሌለው  ነው። ‘ቅዱሳን ያማልዳሉ’ ብሎ ጫት ላይ ሺሻ እየሳበ የሚከራከር ብዙ ሰው አለ። ሕይወቱን ብትጠይቂው ዜሮ ነው።  መጻፍ አለበት ብዬ የማስበው ይሄንን ነገር የሚያስተወው የሚያስጥለው ጽሑፍ ነው።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- አዎ የአንድ ሴት እና የአንድ ወንድ አባት ነኝ። ባለቤቴ መቅደስ ፈለቀ ወርቁ ትባላለች ። የወታደር የሻምበል ባሻ ልጅ ናት። ሦስት ቁጥር ማዞሪያ እያለን ቤታችን ፊትና ጀርባ ነበር፡፡ በመካከላችን የእግርም የመኪናም መንገድ አለ። ኳስ ለመጫወት ስንፈልግ ከቤታችን ወጥተን ከእኛ ቤት ጓሮ ስንሄድ እነሱ ቤት ፊት ለፊት እንሆናለን። እዚያ ፀጉሯ የሚገርም ነው ብን እያረገች ስትሮጥ እስካሁን አይኔ ላይ አለ። ሁሌ እናገረዋለው እና ቆንጆ ናት።

       እሷ ብፁዕ አባታችን ጋር ከሌሎች ልጆች ጋር ሥራ ታግዛለች። ምግብ ትሰራለች ልብሳቸውን ታጥባለች እዛ ታገለግል ነበር። ሴቶችም ኢየሱስ ክርስቶስን በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸውም ያገለግላሉ የሚል ማርቆስ ላይ አለ ። አባታችን ጋር መሄድ ስንጀምር ተቀራረብን። እሷ ቤተሰብ ለመርዳት አረብ ሀገር መሄድ ነበረባት። ልትሄድ ሀያ ሁለት ቀናት ሲቀራት በፍቅር ተዋወቅን መንፈሳዊ ማለት ነው። አረብ ሀገር ቆይታ መጣች ሁለታችንም ቤተሰብ እንረዳ ነበር። ሁለታችንም ስምንት ስምንት እህት ወንድሞች አሉን። ከቤተሰብ እኔ ሦስተኛ ብሆንም መጀመሪያ ገብቼ ተምሬ ተመርቄ ስራ የያዝኩት  እኔ ነበርኩ። እንደዚህ እንደዚህ ብለን ቤተሰቦቻችንን አስተምረን ድረን ኩለን መጨረሻ ላይ እኛ ተጋባን ማለት ነው። ጋብቻችን የተፈፀመው ምሁር ገዳመ ኢየሱስ ነው። እናት አባት የሌላቸው ገዳሙ ሚረዳቸው ልጆች አሉ። በሬውን ለእነሱ አርደን አንድ ሳምንት ቆይተን ተመለስን። ልጆች ወለድን ሴቷ አቢጊያ አያሌው ዘኢየሱስ ትባላለች ዐሥራ አራት ዓመትዋ ነው። ወንዱ ስምንት ዓመቱ ነው፡፡ አናሲሞስ አያሌው ዘኢየሱስ። ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው ። እነዚህ ናቸው ቤተሰቦቼ ።

       ይህ የምንኖርበት ቤት የአቡነ ሺኖዳን መጽሐፍ እየሸጥኩኝ የሠራሁት ቤት ነው ። ግርግዳውን ገለጥ ብታረጊው የዲያቢሎስ ውጊያዎች የእሳቸውን መጽሐፍ ነው ። ወንድሞች እህቶች አሉኝ እሷም እንደዛው ስምንት ስምንት ነን። አሁን በቅርብ ጊዜ እሌኒ ምትባል እህታችን የመጨረሻዋ ትንሽ ታማ አረፈች። እናቴም በሕይወት የለችም አባቴም የለም።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- ሕይወት ደስታም ኀዘንም ነው፡፡ አሁን ቅድም የጠራሁት በተለይ የእናቴ የወንድሜ የሁሉም ያሳዝናል። ሁላችንንም በፍቅር አጥራ ይዛ ያሳደገችን እናታችንን ማጣት ከባድ ነበረ። አሁን ደግሞ የእዚህች የእኅቴ አንድ ዓመት ከሦስት ወር ከባድ ኀዘን ነበረ፡፡ በሕይወት ዘመኔ ያጋጠመኝ የሚያሳዝን ነገሮች እነዚህ ናቸው።

       የሚያስቀኝና የማልረሳው አንድ ቀን ሁሌም አምስት ሰዓት ተኝቼ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ላይ እነሳለው። ጥሩ ሰዓቴ ነው ፤ ሥጋዬ  ስለለመደው እንቅልፌ አይመጣም። አንዴ ግን ማልረሳው እየተረጎምኩኝ ነዉ እየፃፍኩኝ ነው መጽሐፌን ፣ መዝገበ ቃላት፣ የምጽፍበት ኮምፒውተር ይዣለው። ተራ በተራ እያየዋቸው እንደ ሸማኔ መወርወሪያ በአንገቴ ስወዛወዝ ነው የማመሸው ። ታዲያ እየሠራው አንዷን ፊደል ተጭኜ እንቅልፍ ወሰደኝ። ዐሥር ሺህ ገፅ ይሁን አላውቅም ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ስነቃ ብዙ ገጽ በአንድ ፊደል ስሞላ አድሬያለሁ። እሱን እድሜ ልኬን አረሳውም።

        አንዳንዴ የራሳችን ሥራ ይመስለናል እንጂ መንፈሳዊ ሥራ የእግዚአብሔር ነው። የሚገርመው ሥራው ሲሰራ አልጋ በአልጋ አልነበረም። አፋር በረሀ ላይ የተተረጎሙ መጽሐፍቶች አሉ፡፡ ፈተና ይበዛዋል ፣ በሽታ ሊመጣ ይችላል ፤ መጨረሻ ላይ ነው የምነቃው ‘ለካ ይሄን ነገር እየሠራሁ ስለሆነ ነው?’ እላለሁ። “ግራ አዝማች” ዲያብሎስ ይተናኮላል። እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር እየቆየን ስለምናየው ነው እንጂ እርሱ ፈተናዎችን እየተከላከለልን ነው። ካልሆነ መንፈሳዊ ሥራ ለመሥራት በጣም ከባድ ነው።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ:-  አንድ አምስት ስድስት መጽሐፍቼን ያለፈቃድ ተርከውብኛል። ቢቸግረኝ ማስጠንቀቂያ ጻፍኩኝ ፤ ድካምን ባዶ የሚያደርጉ ሰዎች አሉ። እኔ አላየሁትም ነበር። ሰዎች መጥተው ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል። ለምን አትሠራም?  እያሉ ሲጠይቁኝ አሁን በእዚህ ዓመት ትረካውን ጀመርሁ። የገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ልጆች ከህፃናት ክፍል የተሸጋገሩ እነሱ እየሠሩልኝ ነው። በጣም የማመሰግናቸው ልጆች አሉ። መጥራት እችላለሁ?

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ :- ናትናኤል፣ትዕግስት ቴዎድሮስ፣ማዕዶት ሌሎችም ስማቸውን የማላስታውሰው። ተጀምሯል እንግዲህ ‘የተስፋ ሕይወት’ አንድ ክፍል ተጀመሯል። ከሁለት ሰዓት ተኩል እስከ ሦስት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይነበባል።

መምህር አያሌው ዘኢየሱስ:- አንድ መጽሐፍ ይዣለው የአቡነ ሺኖዳን ፤ ከዛ በፊት ደግሞ የተረጎምኳቸው አሉ የራሴም የሕይወት ታሪክ አለኝ ። እጄ ላይ አራት አምስት መጽሐፍቶች አሉ ሠርቼ ያስቀመጥኳቸው ። ማሳተም በጣም ከባድ ስለሆነ ማለት ነው። በገንዘብ ድጋፍ የሚያሳትም ሰው ካላገኘ በጣም ይከብዳል። እግዚአብሔር እየረዳኝ ነው፡፡ በእርሱ ቸርነት ይኸው እዚህ ደርሼያለሁ። ከጎን ደግሞ የትረካው ሥራ አለ። በዚህም ውስጥ እኛና የእግዚአብሔር ጊዜ የሚል በሁለት ክፍል ፣ ‘ጎስቋላው’ የሚል የአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ ሁለት ክፍል ከዛ ደግሞ የተራራው ስብከት፣ የተስፋ ሕይወትን ጀምሬያለው። በሳምንት ሁለት ጊዜ ነው የሚተላለፈው። ‘መምህር አያሌው ዘኢየሱስ ቲዩብ’ በሚለው ቢገባ ይገኛል። ተስፋ ለሰው ልጅ አሁን በእዚህ ሰዓት በጣም ሚያስፈልግ ስለሆነ እሱን ብለን ጀምረነዋል። እነዚ ያለምንም ፈቃድ በድፍረት የሚሠሩትን ደግሞ ትክክለኛውን በስሜ ያለውን ትረካ  እያያቹ ለይታቹ የእኔ መሆኑን አረጋግጣቹ እንድታዳምጡ በዚህ ብትቃወሙልኝ ደስ ይለኛል ።

Share your love

160 አስተያየቶች

  1. ”ሕይወት ነክ መጻሕፍት መብዛት አለባቸው”
    ሙሉውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት በእውነት ትልቅ መምህር ነዎት።
    ዳንደረባዉ ሚዲያ እናመሰግናለን …
    መምህር ቃለህይወት ያሠማልን።

  2. የተቻለንን የገንዘብ መጥተን አዋጥተን ቢያን ከላይ የተጠቀሱትን 5 መጻሕፍት ለማሳተም ስፖንሰር ብንሆን እንደ ኢጃት ቤተሰብ
    #ስፖንሰር እዳልሆን የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

  3. በመጀመሪያ መምህር አያሌው ዘኢየሱስን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ መርመ ግብር እንደተያዘ በማስታወቂያ ስሰማ የፊት ገጻቸውን ለማየት እጅግ ጓግቼ ነበር የሚገርመው እንደጠበኩት አይደለም ማለቴ እንጀ ባሕታውያን አይነት ፀጉር ስመለከት ትኩረቴን ሳበው ለምን ግን አልጠየቃቿቸውም ? ብቻ ደስ የሚል ቃለ መጠይቅ ነበር። በተለይ ደግሞ ዲ/ን ሔኖክ በፌስ ቡክ ገጹ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳን ለመቀበል ሲጠብቁ እንደነበር የሚያሳይ ምስል ለጥፎ ስለነበር እንደው እሳቸውን ሲያዩ ምን ተሰምቷቸው ነበር የሚል ስሜት በውስጤ ተቀርፆ ነበር ብቻ እንደጠበኩት ነው። ከትርጉም ስራዎቻቸው ብዙዎቻን ተምረናል። መምህር አያሌው አለማየሁ ዋሴ እሸቴን (ዶ/ር) ጠቅሰው የሰጡት ምክረ ሐሳብ የሚደገፍና ይበል የሚያሰኝ ነው። የአለማየሁ ዋሴ ድርሰቶች በእድሜ የተገደቡ አይደለም ማለትም በሁሉም እድሜ ክልል ያሉት ሊያነቡት የሚችሉ ዓይነት ድርሰቶች ናቸው። መምህር እንዳሉት ደግሞ እውነትም ደረቅ እውነት ሳይሆን በሕይወት አጋጣሚ የሆን ክስተቶችን ጠንካራውን ብቻ ሳይሆን ድክመትንም ሳይደብቁ በመማርያ መንገድ መጻፋቸው በሰው ዘንድ ተወዳጅ አድርገዋቸዋል።

    ስለሁሉ ስብሐት ለእግዚአብሔር
    እናተም በርቱ ክፍን ያርቅላችሁ
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  4. Загадка истинности в критериях
    истина это в обществознании [url=http://www.koah.ru/koret/74.htm]http://www.koah.ru/koret/74.htm[/url].

  5. በእውነት ብዙ የምንማርበትና የተማርንበት መምህር ነው ዕድሜ ይስጥልን።

  6. መምህር አያሌው ዘኢየሱስ መጽሐፍትን ለመተርጎም ትክክለኛው ሰው ናቸው። በእርሶ ትጋት እኛም ብዙ አትርፈናል።

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  7. Вскрытие замков на металлических дверях в Москве без демонтажа
    вскрытие замков в москве цена [url=http://www.azs-zamok11.ru]http://www.azs-zamok11.ru[/url].

  8. Профессиональные ритуальные услуги по организации погребения
    ритуальные услуги москва [url=https://ritual-gratek17.ru/]https://ritual-gratek17.ru/[/url].

  9. Сантехнические услуги: опытный мастер на все руки
    вызвать сантехника спб [url=https://vyzov-santekhnikaspb.ru]https://vyzov-santekhnikaspb.ru[/url].

  10. Dream Symbols Decoded: Understanding Common Dream Meanings
    christian dream dictionary [url=http://www.dreammeaningworld.com/]http://www.dreammeaningworld.com/[/url].

  11. Энергоэффективные каркасные дома под ключ для экономии
    строительство каркасного домика [url=https://www.karkasnye-doma-pod-klyuch-77.ru/]https://www.karkasnye-doma-pod-klyuch-77.ru/[/url].

  12. Новые тенденции в оформлении окон: электрокарнизы
    электро гардины купить [url=http://prokarniz36.ru/]http://prokarniz36.ru/[/url].

  13. Вывод из запоя: эффективные методы лечения и восстановления
    круглосуточный вывод из запоя самара [url=http://vyvod-iz-zapoya63.ru/]http://vyvod-iz-zapoya63.ru/[/url].

  14. Встречайте новые культуры: захватывающие туры по экзотическим странам
    экскурсионные туры в абхазию [url=https://turandruner.ru/tours/country/abhazia]https://turandruner.ru/tours/country/abhazia[/url].

  15. Мастер по сантехнике: профессиональные услуги для вашего дома
    вызвать сантехника спб [url=http://www.vyzovsantekhnikaspb-1.ru]http://www.vyzovsantekhnikaspb-1.ru[/url].

  16. Amirdrassil Raid Boost: Level-Up Your Gameplay
    amirdrassil boost buy [url=http://www.amirdrassil-boost.com]http://www.amirdrassil-boost.com[/url].

  17. Безопасная уборка после пожара: советы от экспертов
    уборка квартир пожара [url=http://www.uborca-posle-pozhara.ru/]http://www.uborca-posle-pozhara.ru/[/url].

  18. Малоизвестные МФО: Ваш путь к выгодным онлайн займам
    новые мфо онлайн [url=http://novye-maloizvestnye-zajmy.ru/]http://novye-maloizvestnye-zajmy.ru/[/url].

  19. Список МФО: где получить выгодный займ с моментальным одобрением
    список займов на карту [url=https://www.vse-mikrozajmy-spisok.ru/]https://www.vse-mikrozajmy-spisok.ru/[/url].

  20. Профессиональные услуги по ремонту ноутбуков
    сколько стоит ремонт ноутбука [url=https://www.remontnote24.ru]https://www.remontnote24.ru[/url].

  21. Подчеркните свою индивидуальность: стильные женские трусы для уверенности в каждом движении
    купить женские трусы [url=https://zenskie-trusy1.ru]https://zenskie-trusy1.ru[/url].

  22. Пляжная мода 2024 года для женщин: актуальные тренды и стильные купальники
    купальники женские [url=http://kupalniki1.ru/]http://kupalniki1.ru/[/url].

  23. Дизайнерские радиаторы: преимущества и особенности выбора
    дизайнерские радиаторы купить астана [url=https://dizaynerskieradiatory.kz]https://dizaynerskieradiatory.kz[/url].

  24. Дизайнерские радиаторы: особенности и преимущества выбора
    дизайн радиаторы минск [url=https://www.dizaynerskieradiatory.by]https://www.dizaynerskieradiatory.by[/url].

  25. Уборка квартиры в Новосибирске на высшем уровне: с нами Ваш дом будет чистым
    Клининговые услуги [url=https://chisty-list.online/]https://chisty-list.online/[/url].

  26. Как правильно накручивать поведенческие факторы: рекомендации экспертов
    seo накрутка поведенческих факторов [url=http://www.nakrutka-povedencheskih-factorov.ru]http://www.nakrutka-povedencheskih-factorov.ru[/url] .

  27. Вывод из запоя: важность комплексного подхода
    срочный вывод из запоя на дому [url=http://www.vyvod-iz-zapoya063.ru/samara/na-domu/]http://www.vyvod-iz-zapoya063.ru/samara/na-domu/[/url] .

  28. Стационарный вывод из запоя: когда необходимо лечение в клинике
    нарколог на дом в самаре [url=http://www.vyvod-iz-zapoya063.ru/samara/narkolog-na-dom/]http://www.vyvod-iz-zapoya063.ru/samara/narkolog-na-dom/[/url] .

  29. Мойка окон в любое время года: мы работаем всегда
    мойка окон в квартире [url=https://mytie-okon1.ru]https://mytie-okon1.ru[/url] .

  30. Почему важно не откладывать лечение травмы зуба: объясняет эксперт
    лечение травм зубов [url=https://www.ushib-zuba.ru/]https://www.ushib-zuba.ru/[/url] .

  31. Услуги сантехника: оперативное устранение протечек и засоров
    услуги сантехника в спб [url=https://uslugi-santekhnika-1.ru/]https://uslugi-santekhnika-1.ru/[/url] .

  32. Лучшие предложения жилья в Крыму: где искать и как выбирать
    крым цены [url=https://www.otdyh-v-krimy.ru/]https://www.otdyh-v-krimy.ru/[/url] .

  33. Прогнозы и астрологические аспекты: Как готовиться к будущим изменениям
    астрологические аспекты книга http://www.tarosite.ru .

  34. Современные методы лечения зависимости в Перми: наркологическая клиника Пермь
    наркологический центр Пермь http://narkoklin1.ru/ .

  35. Цены на уборку дома в Санкт-Петербурге: прайс-лист и стоимость клининговых услуг
    прайс лист на клининговые услуги https://www.uborka-chistota.ru .

  36. ГК Пересвет: как установить винтовые сваи без ошибок
    ГК Пересвет: стоимость винтовых свай

  37. Как Biohacker Host помогает в улучшении когнитивных способностей с ноотропами
    Biohacker Host: купить ноотропы в Москве

  38. Видеорегистраторы, парктроники и камеры — всё для авто в интернет-магазине ParkCam
    интернет магазины автоэлектроники parkcam ru

  39. Наборы для маникюра Solingen — высококачественные инструменты для ухода за ногтями
    solingen маникюрный набор купить http://www.nozh-kitchen.ru/ .

  40. Производство упаковочных материалов в Красноярске: как выбрать надежного поставщика? Мегапласт
    megaplast megaplast24 ru

  41. Стильные штопоры и открывалки для вина с обрезателями фольги — аксессуары, которые оценит каждый
    штопор электрический купить https://www.vseodlyakuhni.ru .

  42. Опасные бритвы с доставкой — профессиональные инструменты для идеального бритья
    купить опасную бритву для бритья https://pro-nozhi.ru/ .

  43. Современная психиатрическая клиника в СПб: диагностика и лечение психических расстройств
    частная психиатрическая клиника стационар psihiatricheskaya-klinika-spb.ru .

  44. Оперативное оформление пропусков на МКАД для грузовых автомобилей: с нами это просто
    пропуска в москву для грузовиков propuskamos1.ru .

  45. Лизинг оборудования: ключ к успеху вашего бизнеса без крупных инвестиций
    купить оборудование в лизинг oborudovanie-v-lizing.ru .

  46. ЭКО по ОМС в СПб: высококвалифицированные специалисты и современное оборудование
    список анализов для эко по омс 2024 https://embryoscopespb.ru .

  47. Точная спермограмма в СПб: современные методики и профессиональные консультации в одном месте
    анализ спермограммы цена спб http://www.eggdonorsspb.ru/ .

  48. Недорогие модульные дома под ключ: быстровозводимое жильё для загородной жизни
    модульные дома проекты и цены [url=https://modul-stroy-spb.ru/]модульные дома проекты и цены[/url] .

  49. Центр репродуктологии в СПб: высокие технологии, индивидуальный подход и забота о каждом пациенте
    лучшая клиника эко в санкт петербурге https://www.reproductologyonline.ru/ .

አስተያየትዎን ያስቀምጡ

Your የኢሜል አድራሻ አይታተምም። Required fields are marked *